ዘፍጥረት 20:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “በንጹሕ ኅሊና እንዳደረግህ ዐውቄአለሁ፤ ወደ እርስዋ ቀርበህ በእኔ ፊት ኃጢአት እንዳትሠራ ያደረግኩህም ስለዚህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በሕልሙ እንዲህ አለው፤ “አንተ ይህን ያደረግኸው በቅን ልቡና መሆኑን ዐውቄአለሁ፤ በእኔም ላይ ኀጢአት እንዳትሠራ የጠበቅሁህና እንዳትነካትም ያደረግሁት ለዚሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ አወቅሁ፥ እኔም ደግሞ በፊቴ ኃጢአትን እንዳትሠራ ከለከልሁህ፥ ስለዚህም ትነካት ዘንድ አልተውኩህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በሕልም አለው፥ “ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ ዐወቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢአትን እንዳትሠራ ጠበቅሁህ፤ ስለዚህም ትቀርባት ዘንድ አልተውሁህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በሕልም አለው፤ ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ አወቅሁ፥ እኔም ደግሞ በፊቴ ኃጢአትን እንዳትሠራ ከለከልሁህ፤ ስለዚህም ትነካት ዘንድ አልተውሁም። |
ነገር ግን እግዚአብሔር ‘በአትክልቱ ቦታ መካከል ካለው ዛፍ ፍሬ አትብሉ፤ በእጃችሁም አትንኩት፤ ይህን ብታደርጉ ትሞታላችሁ’ ብሎ አስጠንቅቆናል” ስትል መለሰችለት።
ያዕቆብና ልጆቹ ያንን ስፍራ ትተው ለመሄድ ተነሡ፤ እግዚአብሔር በዙሪያቸው በነበሩት ሰዎች ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ስላሳደረባቸው ሊያሳድዱአቸው አልደፈሩም።
ጌታዬ በዚህ ቤት ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ከእኔ የበለጠ ኀላፊነት የለውም፤ ከአንቺ በቀር በእኔ ቊጥጥር ሥር ያላደረገው ምንም ነገር የለም፤ ይኸውም ሚስቱ ስለ ሆንሽ ነው፤ ታዲያ ይህን አስከፊ ኃጢአት በመፈጸም እግዚአብሔርን እንዴት አሳዝናለሁ?”
እኔ ያመፅኩት በአንተ ላይ ነው፤ የበደልኩትም አንተን ብቻ ነው፤ አንተ የምትጠላውን ነገር አደረግሁ፤ ስለዚህ በእኔ ላይ መፍረድህና እኔንም መቅጣትህ ትክክል ነው።
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
አሕዛብን ሁሉ አስወግጄ ግዛታችሁን አሰፋለሁ፤ ስለዚህ በእነዚህ በሦስት በዓላት ወቅት ወደ እኔ ስትቀርቡ አገራችሁን ለመውረር የሚመኝ ማንም አይመጣም።
ከዚህም በላይ ጲላጦስ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ በንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።
ምሥጢራዊው የዐመፅ ኀይል አሁንም በመሥራት ላይ ነው፤ ሆኖም አሁን የሚከለከለው አለ፤ ይህም የሚሆነው ያ የሚከለክለው እስኪወገድ ድረስ ነው።
የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤
በአንቺ ላይ ጒዳት ከማድረስ እግዚአብሔር ጠብቆኛል፤ ፈጥነሽ ወደ እኔ ባትመጪ ኖሮ ግን፥ ከናባል ወንዶች አንድ እንኳ ሳላስተርፍ ከንጋት በፊት ሁሉንም ለመግደል በሕያው እግዚአብሔር ስም ምዬ ነበር።”