Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 6:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ግንኙነት የሚያደርግ እንደዚሁ ነው፤ የሌላውን ሰው ሚስት የሚነካ ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ከሰው ሚስት ጋራ የሚተኛም እንደዚሁ ነው፤ የሚደርስባትም ከቅጣት አያመልጥም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ወደ ሰው ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፥ የሚነካትም ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ወደ ጐልማሳ ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፤ የሚነካትም ሁሉ አይነጻም።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 6:29
19 Referencias Cruzadas  

ስለ ጻፋችሁልኝ ጥያቄ ሰው ከሴት ጋር ግንኙነት ባያደርግ መልካም ነው።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።


አንዳንዶቹ ከጐረቤቶቻቸው ሚስቶች ጋር ያመነዝራሉ፤ ሌሎችም ምራቶቻቸውን ይደፍራሉ፤ እንዲሁም ከአባት የተወለዱትን እኅቶቻቸውን ያረክሳሉ፤


እግዚአብሔር ትምክሕተኞችን ሁሉ ይጸየፋል፤ ከቅጣት እንዲያመልጡም አያደርጋቸውም።


አኪጦፌልም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፦ “ቤት እንዲጠብቁ ከተዋቸው ከአባትህ ቁባቶች ጋር ተገናኝ በዚህም እስራኤላውያን ሁሉ አባትህን እንዳዋረድከው ያውቃሉ፤ ከአንተም ጋር ያሉት ሰዎች ሁሉ ስሜታቸው ይበረታታል።”


አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ቢያመነዝር፤ አመንዝራውና አመንዝራይቱ ሁለቱም በሞት ይቀጡ፤


“የሌላውን ሰው ቤት አትመኝ፤ ሚስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።”


ከሌላ ሰው ሚስት ጋር በመተኛት ራስህን ከእርስዋ ጋር አታርክስ።


እግሩስ ሳይቃጠል ፍም ረግጦ ለመሄድ የሚችል ሰው አለን?


ለእስራኤላውያን ጣዖቶች አይሰግድም፤ ወይም በተከለከሉ መስገጃዎች የተሠዋውን ማንኛውንም ነገር አይመገብም፤ የሌላ ሰው ሚስትን አይደፍርም፤ ወይም የወር አበባ ከታያት ሴት ጋር ግንኙነት አያደርግም፤


በሰይፋችሁ ትተማመናላችሁ፤ አጸያፊ ነገር ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዱ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ዝሙት ይፈጽማል፤ ታዲያ፥ ምድሪቱ እንዴት የእኛ ርስት ናት ትላላችሁ?’


አብርሃም ሚስቱን ሣራን እኅቴ ናት አለ፤ ስለዚህ የገራራ ንጉሥ አቤሜሌክ ሰዎች ልኮ ሣራን እንዲያመጡለት አደረገ።


የሐዘንዋም ጊዜ ሲፈጸም ዳዊት ሰው ልኮ ወደ ቤተ መንግሥት አስመጣት፤ ለእርሱም ሚስት ሆና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር እግዚአብሔርን አሳዘነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios