ቈላስይስ 1:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሚሆነው በእምነታችሁ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በመቆም ከሰማችሁት የወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው። እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ የተሰበከውም ወንጌል ይኸው ነው፤ እኔም ጳውሎስ ለዚህ ወንጌል አገልጋይ ሆንሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት የምትጸኑ ከሆነ ነው፤ ይህም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ከሰማችሁት ከሰማይ በታች በመላው ዓለም ከተሰበከው እኔ ጳውሎስም አዋጅ ነጋሪና መልእክተኛ ሆኜ ከተሾምሁለት፥ ከወንጌል ትምህርት ተስፋ የመሠረታችሁ አቅዋም ሳይናወጥ ጨክናችሁ በሃይማኖት ብትጸኑ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም፥ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በሃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል፤ ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፥ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ። |
እርሱ በጥልቅ ቆፍሮ ቤቱን በጽኑ አለት ላይ የመሠረተውን ሰው ይመስላል፤ ጐርፍ መጥቶ ያንን ቤት ገፋው፤ ነገር ግን በጽኑ መሠረት ላይ ስለ ተሠራ ሊያነቃንቀው አልቻለም።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ፥ በሰማርያ፥ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
እርሱም ሄዶ እግዚአብሔር ጸጋውን ለሕዝቡ እንዴት እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉም በሙሉ ልብ ጸንተው ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲኖሩም መከራቸው።
በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።
የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም።
አሁን ግን ተነሥና በእግርህ ቁም፤ እኔ የተገለጥኩልህ አሁን እኔን ባየህበትና ወደፊትም እኔ ለአንተ በምገለጥበት ነገር አገልጋይና ምስክር እንድትሆነኝ ልሾምህ ፈልጌ ነው።
ስለዚህ መዳን ከእርሱ በቀር በሌላ በማንም የለም፤ እኛ ልንድንበት የሚገባን እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ስም ከእርሱ በቀር በመላው ዓለም ማንም የለም።”
እስቲ ልጠይቅ፤ ታዲያ፥ ቃሉን አልሰሙም ማለት ነውን? በቅዱስ መጽሐፍ፥ “ድምፃቸው በዓለም ሁሉ ተሰማ፤ ቃላቸውም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ በእርግጥ ሰምተዋል።
ይህም ጸጋ የተሰጠኝ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለአሕዛብ በማብሠር እንደ ካህን ሆኜ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል ነው፤ ስለዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰና እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ አገለግላለሁ።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? እነርሱ እናንተ እንድታምኑ ያደረጉአችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ እያንዳንዳቸው የሚያገለግሉትም ጌታ ለያንዳንዳቸው በመደበላቸው ሥራ ነው፤
እኔ ጳውሎስ በእናንተ ፊት ሳለሁ ትሑት ተባልኩ፤ ከእናንተ ስርቅ ግን በእናንተ ላይ ደፋር ተባልኩ፤ በክርስቶስ ቸርነትና ደግነት እለምናችኋለሁ፤
እነርሱ የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን? እኔ ከእነርሱ ይበልጥ የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ፤ ይህንንም ስል እንደ እብድ ሆኜ ነው የምናገረው፤ ከእነርሱ ይበልጥ ብዙ ጊዜ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገርፌአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ለሞት አደጋ ደርሼአለሁ፤
የሐዲስ ኪዳኑ አገልጋዮች እንድንሆን ብቃትን የሰጠን እርሱ ነው፤ ይህም በፊደል በተጻፈው ሕግ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ነው፤ በፊደል የተጻፈው ሕግ ሞትን ያመጣል፤ መንፈስ ቅዱስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
ለምን ዐይነት ተስፋ እንደ ተጠራችሁና ቅዱሳን የሚወርሱት ክቡር ርስት ምን ያኽል ብዙ እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልቡናችሁ ዐይን እንዲበራላችሁ እጸልያለሁ።
የተለያዩት የሰውነት ክፍሎች የሚገጣጠሙት በክርስቶስ ነው፤ አካልም በሙሉ የተያያዘው በመገጣጠሚያዎቹ ነው፤ ስለዚህ እያንዳንዱ የአካል ክፍል የተመደበለትን ተግባር በሚገባ ሲያከናውን አካል በሙሉ ያድጋል፤ በፍቅርም ይታነጻል።
በሰማይ ላይ የምታዩአቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ወይም ከዋክብትን ወይም የሰማይን ሠራዊት ሁሉ በማምለክና ለእነርሱ በመስገድ እንዳትፈተኑ ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን ሁሉ ሌሎች ሕዝቦች ብቻ ያመልኩአቸው ዘንድ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።
በዚህ ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ በትዕግሥት መጠበቅ ባለመቻሌ ስለ እምነታችሁ ማወቅ ፈልጌ ጢሞቴዎስን ወደ እናንተ ላክሁት፤ እርሱን የላክሁትም ምናልባት ፈታኙ በአንድ መንገድ ፈትኖአችሁ ይሆናል፤ ሥራችንም ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል በማለት ፈርቼ ነው።
እኛ ግን የብርሃን ሰዎች ስለ ሆንን ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር፤ እምነትንና ፍቅርን እንደ ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንን ተስፋ እንደ ራስ ቊር እንልበስ፤
እኔም እምነትንና እውነትን ለማብሠር ሐዋርያና አስተማሪ ሆኜ ወደ አሕዛብ የተላክሁት በዚህ ምክንያት ነው፤ ይህንንም ስል እውነት እናገራለሁ እንጂ አልዋሽም።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።
ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ የሆነው እንደ ልጅ ሆኖ ነው፤ ቤቱም እኛ ነን፤ ቤቱ የምንሆነውም የምንተማመንበትን ነገርና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ ነው።
እንግዲህ ሰማያትን ዘልቆ ወደ ላይ ወደ ሰማይ የወጣ ታላቅ የካህናት አለቃ ስላለን እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ፤ የካህናት አለቃውም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤
ከክርስቶስ የተቀበላችሁት መንፈስ በውስጣችሁ ስለሚኖር ሌላ አስተማሪ አያስፈልጋችሁም፤ እርሱ ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ የሚያስተምራችሁም እውነትን ነው እንጂ ሐሰትን አይደለም። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንዳስተማራችሁ በክርስቶስ ኑሩ።
ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ፤ እነሆ፥ እንድትፈተኑ ከእናንተ አንዳንዶቹን ዲያብሎስ ወደ እስር ቤት ያገባችኋል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ የሕይወት አክሊል እሰጥሃለሁ።