Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ቆሮንቶስ 3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች

1 እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን?

2 ሰው ሁሉ የሚያውቃችሁና የሚያነባችሁ በልባችን የተጻፋችሁ የድጋፍ ደብዳቤዎቻችን እናንተ ናችሁ።

3 እናንተስ በእኛ አገልግሎት የመጣችሁ የክርስቶስ መልእክት መሆናችሁ ግልጥ ነው፤ ይህም መልእክት የተጻፈው በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፤ እንዲሁም በሰው ልብ ጽላት ላይ እንጂ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈ አይደለም።

4 ይህን የምንልበት ምክንያት በክርስቶስ አማካይነት በእግዚአብሔር ላይ እምነት ስላለን ነው።

5 አገልግሎታችንን መፈጸም እንድንችል ብቁ የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው እንጂ እኛስ በገዛ ራሳችን ምንም ለማድረግ ብቁ አይደለንም።

6 የሐዲስ ኪዳኑ አገልጋዮች እንድንሆን ብቃትን የሰጠን እርሱ ነው፤ ይህም በፊደል በተጻፈው ሕግ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ነው፤ በፊደል የተጻፈው ሕግ ሞትን ያመጣል፤ መንፈስ ቅዱስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።

7 ሕግ የተቀረጸው በድንጋይ ጽላት በፊደል ነበር፤ ሕግ በተሰጠበትም ጊዜ የነበረው ብርሃን እየተወገደ የሚሄድ ቢሆንም እስራኤላውያን የሙሴን ፊት ትኲር ብለው ሊመለከቱት አልቻሉም፤ እንግዲህ ሞትን ያመጣ ሕግ በእንዲህ ዐይነት ክብር ከተገለጠ

8 ታዲያ፥ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚገኘው አገልግሎት የበለጠ ክብር አይኖረውምን?

9 ሰዎች የተኰነኑበት አገልግሎት ይህን ያኽል ክብር ካለው ሰዎች የሚጸድቁበት አገልግሎትማ እንዴት እጅግ የበለጠ ክብር አይኖረውም?

10 የኋለኛው ክብር እጅግ የላቀ ከመሆኑ የተነሣ ያለፈው ክብር ምንም እንዳልነበረው ይቈጠራል።

11 ያ እየደበዘዘ ይሄድ የነበረው ነገር ይህን ያኽል ክብር ከነበረው፥ ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖረው ነገርማ እንዴት እጅግ የበለጠ ክብር አይኖረውም!

12 እንዲህ ዐይነቱ ተስፋ ስላለን በድፍረት እንናገራለን።

13 ሙሴ እየከሰመ የሚሄደው የፊቱ መንጸባረቅ እስኪወገድ ድረስ እስራኤላውያን እንዳያዩ ፊቱን ይሸፍን ነበር፤ እኛ ግን እንደ እርሱ አይደለንም።

14 የእነርሱ ልቡና በእርግጥ ደንዝዞአል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት ሲያነብቡ ልቡናቸው በዚያው መሸፈኛ እንደ ተሸፈነ ነው። ይህም የሚሆነው ያ መሸፈኛ የሚወገደው በክርስቶስ ብቻ ስለ ሆነ ነው።

15 ዛሬም እንኳ ቢሆን የሕግ መጻሕፍትን ባነበቡ ቊጥር ልቡናቸው በመሸፈኛው ይሸፈናል።

16 ነገር ግን ሰው ወደ ጌታ ሲመለስ “መሸፈኛው ይወገዳል።”

17 ጌታ መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት ነጻነት አለ።

18 እኛ ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት ሆነን በመስታዋት እንደሚታይ ዐይነት የጌታን ክብር እናንጸባርቃለን፤ እኛም መንፈስ የሆነውን የጌታን መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos