Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጴጥሮስ 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ ከምሕረቱ ብዛት በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይመስገን፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3-5 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3-5 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።

Ver Capítulo Copiar




1 ጴጥሮስ 1:3
56 Referencias Cruzadas  

ዳግመኛ የተወለዳችሁት ሕያው በሆነውና ለዘለዓለም ጸንቶ በሚኖረው በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤


የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል፤ ዓለምን የምናሸንፈውም በእምነታችን ነው።


ተስፋችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እያደገ እንዲሄድ የተስፋ አምላክ በእርሱ በመታመናችሁ ደስታንና ሰላምን በሙላት ይስጣችሁ።


ከእግዚአብሔር ጸጋ ሙላት የተነሣ በልጁ ደም ተዋጅተን የኃጢአታችንን ይቅርታ አገኘን።


ለምሕረት አባትና መጽናናትን ሁሉ ለሚሰጥ እንዲሁም ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አባት ለእግዚአብሔር፥ ምስጋና ይሁን።


ይህ እንደሚሆን በክርስቶስ ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ ክርስቶስ ንጹሕ እንደ ሆነ እርሱም ራሱን ንጹሕ ያደርጋል።


በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ታገሡ፤ ሁልጊዜ ጸልዩ።


እርሱ ጻድቅ መሆኑን ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ መሆኑን ዕወቁ።


በሰማይ ባለው መንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።


እግዚአብሔር በፊቱ ሲያልፍ እንዲህ ብሎ ዐወጀ፤ “እኔ እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሐሪ አምላክ ነኝ፤ እኔ ለቊጣ የዘገየሁ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅሬና ታማኝነቴ የበዛ ነው፤


ስለዚህ በእኛ ውስጥ በሚሠራው ኀይሉ አማካይነት ከምንለምነውና ከምናስበው በላይ እጅግ አትረፍርፎ ሊያደርግ ለሚቻለው አምላክ፥


ክብር የሚገባው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን በይበልጥ ታውቁ ዘንድ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ።


ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድን የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን መሐሪና ርኅሩኅ ለቊጣ የዘገየህ፥ የተትረፈረፈ ፍቅርና ታማኝነት ያለህ አምላክ ነህ።


የአምላካችን ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ የእኛ ከሆነው እምነትና ፍቅር ጋር ተትረፍርፎ ተሰጠኝ።


ነገር ግን የእግዚአብሔር ምሕረቱ ብዙ ከመሆኑና ለእኛም ያለው ፍቅር ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ


እግዚአብሔር የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን።


በዚህ ዐይነት የተባረከውን ተስፋችንን እንዲሁም የታላቁ አምላካችንን፥ የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በክብር መገለጥ እንጠባበቃለን።


ነገር ግን ክርስቶስ ለሞቱት ከሞት የመነሣት በኲር ሆኖ በእርግጥ ከሞት ተነሥቶአል።


እንግዲህ እምነት፥ ተስፋ፥ ፍቅር፥ እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ነገር ግን ከእነዚህ መካከል የሚበልጠው ፍቅር ነው።


የእግዚአብሔር ባሕርይ በውስጡ ስለሚኖርና ከእግዚአብሔርም ስለ ተወለደ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ኃጢአት አይሠራም፤ ሊሠራም አይችልም።


አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ወተት እንደሚመኙ እናንተም ለመዳን እያደጋችሁ የምትሄዱበትን ንጹሑን መንፈሳዊ ትምህርት ተመኙ።


ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ የሆነው እንደ ልጅ ሆኖ ነው፤ ቤቱም እኛ ነን፤ ቤቱ የምንሆነውም የምንተማመንበትን ነገርና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ ነው።


በአምላካችንና በአባታችን ፊት እምነታችሁ የሚሠራውን፥ ለፍቅር የምታደርጉትንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ተስፋ በትዕግሥት መጠባበቃችሁን ሳናቋርጥ እናስታውሳለን።


እግዚአብሔርም ለቅዱሳኑ ሊገልጥላቸው የፈቀደው ያለውን የዚህን ምሥጢር የክብር ብልጽግና በእናንተ በአሕዛብ መካከል ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።


እኛ የዳንነው በዚሁ ተስፋ ነው። ነገር ግን ተስፋ የምናደርገው ነገር የሚታይ ከሆነ ተስፋ መሆኑ ይቀራል፤ የሚታየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል?


ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት ያስነሣው አምላክ በውስጣችሁ በሚኖረው መንፈሱ አማካይነት ለሟች ሥጋችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።


እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከሰው ዘር፥ ማለትም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከሰው ፈቃድ አልተወለዱም።


እንዲህም ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦ “እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን እንደምታደርግ ገና በአገሬ ሳለሁ ተናግሬ አልነበረምን? ከፊትህ ኰብልዬ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ያቀድኩትም በዚህ ምክንያት ነበር፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ በዘለዓለማዊ ፍቅር የተመላህ፥ ቊጣህን መልሰህ ምሕረት የምታደርግ አምላክ መሆንህን ዐውቅ ነበር።


ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤ እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ! አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።


የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሚጠብቀው የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሁሉ ኀጢአት እንደማይሠራ እናውቃለን፤ ሰይጣንም አይነካውም።


ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን የሚያምን ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ አባቱን የሚወድ ሁሉ ልጁንም ይወዳል።


ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።


እኛ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነን ሳለ በልጁ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀናል፤ አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን በኋላ በልጁ ሕይወት አማካይነት ይበልጡን እንድናለን።


ይህ ጌታችን ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ለሞት ተላልፎ የተሰጠውና እኛንም ለማጽደቅ ከሞት የተነሣው ነው።


ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ቸርና መሐሪ ነህ፤ ወደ አንተ ለሚጸልዩትም ሁሉ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ታሳያቸዋለህ።


ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! አሜን! አሜን!


ከዚህ በኋላ ዳዊት ሕዝቡን “አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ!” አለ፤ መላው ጉባኤም የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ወደ መሬት ለጥ ብለውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ለንጉሡም ክብር ሰጡ።


“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን አጽንቶ ጠብቆአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦


ወዳጆች ሆይ! ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ እርስ በርሳችን እንፋቀር፤ የሚያፈቅር ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል።


ወንድሞች ሆይ! ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ስለ ሞቱት ሰዎች እውነቱን እንድታውቁ እንወዳለን።


ይህን መመሪያ ለሚከተሉ ሁሉና የእግዚአብሔር ወገኖች ለሆኑት እስራኤላውያን ሰላምና ምሕረት ይሁን።


ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን፥ በጸጋውም የዘለዓለም መጽናናትን፥ መልካም ተስፋንም የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን


ስለዚህ ልቡናችሁን አንቅታችሁ ለሥራ ተዘጋጁ፤ በመጠን ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ለምታገኙት ጸጋ ሙሉ ተስፋ ይኑራችሁ።


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።


በቀድሞ ጊዜ ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ፥ የተቀደሱ ሴቶች ያጌጡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ ለባሎቻቸውም ይታዘዙ ነበር።


ጌታ ክርስቶስን በልባችሁ አክብሩት፤ ለሕይወታችሁም ጌታ አድርጉት፤ በእናንተ ስላለውም ተስፋ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁዎች ሁኑ።


ንጉሥ ሕዝቅያስና ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች መጥተው፥ እጅግ የበዛውን የስጦታ ክምር ባዩ ጊዜ፥ እግዚአብሔርንና የእርሱ ወገኖች የሆኑትን የእስራኤልን ሕዝብ አመሰገኑ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios