የዓክቦር ልጅ በኣል-ሐናንም ሞተ፥ በስፍራውም ሃዳር ነገሠ፥ የከተማውም ስም ፋዑ ነው፥ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ ማጥሬድ የወለደቻት መሄጣብኤል ትባል ነበር።
ነህምያ 6:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ወደ ሜሔጣብኤል ልጅ፥ ወደ ዴላያ ልጅ፥ ወደ ሼማዕያ ቤት ሄድሁ፤ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፦ “በእግዚአብሔር ቤት፥ በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ፥ የመቅደሱንም በሮች እንዝጋ፤ ሊገድሉህ ይመጣሉና፥ በሌሊት ሊገድሉህ ይመጣሉና” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ቀን ቤቱ በላዩ ላይ ተዘግቶበት ወደ ነበረው ወደ መሄጣብኤል ልጅ ወደ ድላያ ልጅ ወደ ሸማያ ሄድሁ፤ እርሱም፣ “ሰዎች ሊገድሉህ ይመጣሉ፤ በርግጥም በሌሊት ሊገድሉህ ይመጣሉ፤ በእግዚአብሔር ቤት ባለው በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንገናኝ፤ የቤተ መቅደሱንም በሮች እንዝጋቸው” አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ጊዜ ከቤቱ እንዳይወጣ ተዘግቶበት ወደነበረው የመሄጣብኤል የልጅ ልጅ ወደ ሆነው ወደ ደላያ ልጅ ሸማዕያ ዘንድ ሄድኩ፤ እርሱም “በሌሊት ሊገድሉህ ስለሚመጡ አንተና እኔ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብተን በሮቹን በመዝጋት እንደበቅ” አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ወደ መሔጣብኤል ልጅ ወደ ዶልያ ልጅ ወደ ሴሜይ ቤት ገባሁ፤ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፥ “በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንግባ፤ የመቅደሱንም ደጆች እንዝጋ፤ እነርሱ በሌሊት ይገድሉህ ዘንድ ይመጣሉና” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ወደ መሔጣብኤል ልጅ ወደ ድላያ ልጅ ወደ ሸማያ ቤት ገባሁ፥ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፦ በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ የመቅደሱንም ደጆች እንዝጋ፥ እነርሱ መጥተው ይገድሉሃልና፥ በሌሊትም ይገድሉህ ዘንድ ይመጣሉና አለ። |
የዓክቦር ልጅ በኣል-ሐናንም ሞተ፥ በስፍራውም ሃዳር ነገሠ፥ የከተማውም ስም ፋዑ ነው፥ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ ማጥሬድ የወለደቻት መሄጣብኤል ትባል ነበር።
መላው የአክዓብ ቤተሰብና ትውልዱ ሁሉ መሞት አለባቸው፤ እኔ ከእርሱ ቤተሰብ ወንድ የሆነውን ማንኛውንም ባርያም ሆነ ነጻ ሰው አስወግዳለሁ።
ደግሞም ዋና የመግቢያ ደጆችን ዘጉ፥ መብራቶቹንም አጥፍተዋል፥ በመቅደሱም ውስጥ ለእስራኤል አምላክ አላጠኑም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አላቀረቡም።
ወደ አለቆቹም ወደ ኤሊዔዘር፥ አሪኤል፥ ሽማዕያ፥ ኤልናታን፥ ያሪብ፥ ኤልናታን፥ ናታን፥ ዘካርያስ፥ ሜሹላምና እንዲሁም ወደ መምህራኑ ወደ ዮያሪብና ኤልናታን ላክሁ።
“በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ መካከል በሮችን የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥” ይላል የሠራዊት ጌታ። ቁርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም።