ዘፍጥረት 36:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 የዓክቦር ልጅ በኣል-ሐናንም ሞተ፥ በስፍራውም ሃዳር ነገሠ፥ የከተማውም ስም ፋዑ ነው፥ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ ማጥሬድ የወለደቻት መሄጣብኤል ትባል ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም39 የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማዪቱም ስም ፋዑ ነው፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን፣ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 የዐክቦር ልጅ ባዓል ሐናንም በሞተ ጊዜ ሀዳር በእርሱ እግር ተተክቶ ነገሠ፤ የነገሠባትም ከተማ ፋዑ ትባል ነበር፤ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ ማጥሬድ የወለደቻት መሄጣብኤል ትባል ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 የአክቦር ልጅ በአልሐናንም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ አዳር ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፎጎር ነው፤ ሚስቱም የሜዛአብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ምኤጠብኤል ትባላለች። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 የዓክቦር ልጅ በኣልሐናንም ሞተ በስፍራውም ሃዳር ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ነው ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት መሄጣብኤል ትባላለች። Ver Capítulo |