ዘፀአት 27:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተውጭ ይኸውም ከምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት፣ አሮንና ወንድ ልጆቹ መብራቶቹን ከምሽት እስከ ንጋት በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንና ልጆቹ ከምሽት እስከ ንጋት ይበራ ዘንድ የእግዚአብሔር መገኛ ከሆነው ፊት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ካለው መጋረጃ ውጪ ያኑሩት፤ ይህም በእስራኤል ሕዝብና ወደፊትም በሚነሣው ትውልድ ዘንድ ቋሚ ሥርዓት ሆኖ ይኑር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት ባለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት እንዲበራ ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘላለም ሥርዓት ይሁን። |
በየጥዋቱና በየማታውም ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መዓዛው ያማረ ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የተቀደሰውንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የጌታን ትእዛዝ እንጠብቃለን፥ እናንተ ግን ትታችሁታል።
ኃጢአት እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም በመቅደሱ ሊያገለግሉ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናሉ፤ ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
የማንሣት ቁርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የሰላም መሥዋዕታቸው የማንሣት ቁርባን ይሆናል፤ ለጌታ የማንሣት ቁርባን ይሆናል።
ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታደቀዋለህም፥ ከእርሱም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። ለእናንተም ፍጹም ቅዱስ ይሆንላችኋል።
“እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው፤
ይህም አንድ ጊዜ በዓመት ለእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸው ሁሉ ለማስተሰረይ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆንላችኋል።” ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረገ።
ስለዚህ ተከትለዋቸው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት ከእንግዲህ ወዲህ መሥዋዕታቸውን አይሠዉም። ይህ ለእነርሱ ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።
የአምላካችሁን ቁርባን እስከምታመጡበት እስከዚህ ቀን ድረስ እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።
በዚያም ቀን ታውጃላችሁ፤ የተቀደሰ ጉባኤም ታደርጋላችሁ። የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።
አሮን ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከምስክሩ መጋረጃ ውጭ በጌታ ፊት ሁልጊዜ ያዘጋጀው፤ ለዘለዓለም ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ይሁን።
እርሱም ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ለጌታም በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ውስጥ በዘለዓለም ሥርዓት፥ ለእርሱ እጅግ ቅዱስ የሆነ ድርሻ ነውና በተቀደሰ ስፍራ ይብሉት።”
እጁንም ለቁርባን ባቀረበው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛውም ድንኳን ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
ካህኑም ከእህሉ ቁርባን መልካሙን ዱቄት ከዘይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ እንዲሁም በእህሉ ቁርባን ላይ ያለውን ዕጣን ሁሉ ያነሣል፥ ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
ሌዋውያን ግን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያገለግላሉ፥ እነርሱም የራሳቸውን በደል ይሸከማሉ፤ ለልጅ ልጃችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ በእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም።
ይህም ለእነርሱ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ ከርኩሰት የሚያነጻውን ውኃ የሚረጨው ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ከርኩሰትም የሚያነጻውን ውኃ የሚነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።
ደግሞም ይህን የበለጠ የሚያረጋግጥ የነቢያት ቃል አለ፤ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚያስተውል ቃሉን ልብ በማለት መልካም ታደርጋላችሁ።
“በኤፌሶን ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፦