Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 28:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ኃጢአት እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም በመቅደሱ ሊያገለግሉ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናሉ፤ ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 አሮንና ወንድ ልጆቹ ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ በደል ፈጽመው እንዳይሞቱ እነዚህን መልበስ አለባቸው። “ለአሮንና ለትውልዶቹ ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 አሮንና ልጆቹ ዘወትር ወደ ድንኳን ሲገቡ ወይም በተቀደሰው ስፍራ በክህነት ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ ይለብሱታል፥ በዚህ ዐይነት የውስጥ ሰውነታቸው ስለማይጋለጥ ከሞት ይድናሉ፤ ይህ እንግዲህ ለአሮንና ለትውልዱ ሁሉ ጸንቶ የሚኖር ሥርዓት ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እን​ዲ​ሁም ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ እን​ዳ​ይ​ሞ​ቱም፥ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ሲገቡ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱም ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ወደ መሠ​ዊ​ያው ሲቀ​ርቡ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ላይ ይሆ​ናል፤ ለእ​ርሱ፥ ከእ​ር​ሱም በኋላ ለዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው እንዳይሞቱም፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 28:43
18 Referencias Cruzadas  

ኃፍረተ ሥጋህ በእርሱ ላይ እንዳይገለጥ ወደ መሠዊያዬ በደረጃ አትውጣ።’”


ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”


እንዳይሞቱ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡ፤ ይህም ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆንላቸዋል።”


ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፤ በውስጠኛው አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ ባገለገሉ ጊዜ አንዳች የበግ ጠጉር በላያቸው አይሁን።


እንዳይሞትም የጢሱ ደመና በምስክሩ ላይ ያለውን የስርየት መክደኛ እንዲሸፍን በጌታ ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ያደርጋል።


ስለዚህ ተከትለዋቸው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት ከእንግዲህ ወዲህ መሥዋዕታቸውን አይሠዉም። ይህ ለእነርሱ ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።


ካህናቱ የእስራኤል ልጆች ለጌታ የሚያቀርቡትን የተቀደሰውን ነገር አያርክሱ፤


ባረክሱት ጊዜ እንዳይሞቱ ስለ እርሱም ኃጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ትዛዝን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝ።


በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ ፈጽሞ ማንኛውንም ስብና ደም እንዳትበሉ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።”


“ማንም ሰው የመሓላን ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ ወይም ስለ ነገሩ አይቶ ወይም አውቆ ባይናገር፥ ኃጢአት መሥራቱ ነውና በደሉን ይሸከማል።


“ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ ጌታም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል።


ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ ለጉባኤው ሁሉ አንድ ዓይነት ሥርዓት ይኑር፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁት መጻተኛውም በጌታ ፊት እንዲሁ ይሆናል።


ከዚህም በኋላ ኃጢአትን እንዳይሸከሙ እንዳይሞቱም፥ የእስራኤል ልጆች ወደ መገናኛው ድንኳን አይቅረቡ።


የተመረጠውንም ከእርሱ ባቀረባችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤልን ልጆች የተቀደሱ ነገሮች አታረክሱም።’ ”


ጌታም አሮንን ተናገረው እንዲህም አለው፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ የቀደሱትን እንደ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባኔን ሁሉ ለአንተ እንድትጠብቀው ሰጥቼሃለሁ፤ ለአንተና ለልጆችህ የክህነትህ ድርሻ እንዲሆን ለአንተ የተገባህ አድርጌ ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ።


ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመንገድም ላይ ያልሆነ የፋሲካን በዓል ባያከብር፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ የጌታን ቁርባን በተወሰነለት ጊዜ አላቀረበምና ያ ሰው ኃጢአቱን ይሸከማል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos