ዘሌዋውያን 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ካህኑም ከእህሉ ቁርባን መልካሙን ዱቄት ከዘይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ እንዲሁም በእህሉ ቁርባን ላይ ያለውን ዕጣን ሁሉ ያነሣል፥ ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ካህኑ ከላመው ዱቄትና ከዘይቱ አንድ ዕፍኝ ያንሣለት፤ በእህሉ ቍርባን ላይ ያለውንም ዕጣን በሙሉ ይውሰድ፤ ይህንም፣ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ፣ ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ከዚህም በኋላ ካህኑ ዘይት ካለበት ከላመ ዱቄት በእፍኙ ወስዶና በእህሉ መባ ላይ ያለውን ዕጣን በሙሉ አንሥቶ ለእግዚአብሔር ያቀረበ መሆኑን ለማሳወቅ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ የዚህም መሥዋዕት መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ካህኑም ከእህሉ ቍርባን መልካሙን የስንዴ ዱቄት ከዘይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ ደግሞም በእህሉ ቍርባን ላይ ያለውን ዕጣን ሁሉ ያነሣል፤ ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ ያለው የመታሰቢያ ቍርባን እንዲሆን ለመታሰቢያ ነውና በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ካህኑም ከእህሉ ቍርባን መልካሙን ዱቄት ከዘይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ ደግሞም በእህሉ ቍርባን ላይ ያለውን ዕጣን ሁሉ ያነሣል፥ ለእግዚአብሔርም ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። Ver Capítulo |