Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 28:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት እንዲሆኑልኝ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን አቅርብ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ ከእስራኤላውያን መካከል ወንድምህ አሮንን ከወንዶች ልጆቹ ከናዳብ፣ ከአብዩድ፣ ከአልዓዛርና ከኢታምር ጋራ ወደ አንተ አቅርባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ወንድምህን አሮንንና ልጆቹን ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን ወደ አንተ አቅርብ፤ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝም ዘንድ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ለያቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ​ተህ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅ​ርብ፤ አሮ​ንን የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች፥ ናዳ​ብን፥ አብ​ዩ​ድ​ንም፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ኢታ​ም​ር​ንም አቅ​ርብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት ይሆኑልኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን አብዩድንም አልዓዛርንም ኢታምርንም፥ አቅርብ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 28:1
33 Referencias Cruzadas  

የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ከሁሉ በላይ የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፥ እርሱና ልጆቹ፥ ለዘለዓለም በጌታ ፊት እንዲያጥኑና እንዲያገለግሉ፥ በስሙም ለዘለዓለም እንዲባርኩ ተለይተው ነበር።


ዮሐናንም ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በሠራው ቤት በክህነት ያገለግል ነበረ፤


የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥


የጌታም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


የአሮን ቤት ሆይ፥ በጌታ ታመኑ፥ ረድኤታቸውና መከታቸው እርሱ ነው።


ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው፥ ጌታን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።


ሙሴንም እንዲህ አለው፦ “አንተ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወደ ጌታ ውጡ፥ በሩቁም ስገዱ፤


ሙሴ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወጡ፤


ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን እነዚህን አልብሳቸው፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፥ እጆቻቸውንም ታነጻለህ፥ ትቀድሳቸዋለህም።


“ለእኔ ካህናት እንዲሆኑ እንድትቀድሳቸው የምታደርገው ነገር ይህ ነው፤ አንድ ወይፈንና ነውር የሌለባቸውን ሁለት አውራ በጎች ውሰድ።


የመገናኛውን ድንኳንና መሠዊያውን እቀድሳለሁ፤ በክህነትም እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን እቀድሳለሁ።


አሮንንና ልጆቹን በመታጠቂያ ታስታጥቃቸዋለህ፥ ቆብን ታለብሳቸዋለህ፤ ክህነትም ለዘለዓለም ለእነርሱ የተወሰነ ይሆናል፥ እንዲሁም አሮንን እጅና የልጆቹን እጅ ትቀድሳለህ።


አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፥ ካህነት ሆነው እንዲያገለግሉኝም ቀድሳቸው።


በብልሃት የተሠራውን ልብስ፥ በክህነት እኔን የሚያገለግሉበትን የካህኑ የአሮን የተቀደሱ ልብሶች የልጆቹ ልብሶች፥


በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች።”


አሮንም የዓሚናዳብን ልጅ የናሕሾንን እኅት ኤሊሼባን አገባ፥ እርሷም ናዳብ፥ አቢሁ፥ ኤልዓዛርንና ኢታማርን ወለደችለት።


የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በጌታም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደውን እሳት አቀረቡ።


ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትንም ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እጅግ የተቀደሰ ነውና ለጌታ ከሆነው በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የተረፈውን የእህሉን ቁርባን ውሰዱ፥ እርሾም ያልገባበት ቂጣ አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤


“ጌታን በክህነት እንዲያገለግሉት እነርሱን ባቀረባቸው ቀን ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይህ ነው።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


“አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅባቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሚቀርበውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ የሚቀመጥበትንም መሶብ ውሰድ፤


አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ለመሠዊያው የሚደረገውን ነገር ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን እንድታደርጉ የክህነታችሁን ግዴታዎች በትጋት ፈጽሙ፥ አገልግሉም፤ ክህነታችሁን እንደ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው ቢቀርብ ይገደል።”


ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።


በጌታም ፊት ያልተፈቀደውን እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ።


እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት በክህነት ሲያገለግል፥


እስራኤላዊያንም ከብኤሮት ብኔያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም እዚያ ሞቶ፥ እዚያው ተቀበረ፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ።


በጌታ ስም ቆሞ ለዘለዓለም ያገለግል ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጦአል።


ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆነኝ ዘንድ፥ በመሠዊያዬ ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣንንም ያጥን ዘንድ ኤፋድንም በፊቴ እንዲለብስ ለእኔ መረጥሁት፤ የእስራኤልንም ልጆች የሚያቀርቡትን የሚቃጠል መሥዋዕት ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos