ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ በዚህም ጊዜ “እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።
ዘኍል 34:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰዎቹም ስም ይህ ነው፤ ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስማቸውም ይህ ነው፤ “ከይሁዳ ነገድ፣ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰዎቹም ስም ይህ ነው፤ ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰዎቹም ስም ይህ ነው፤ ከይሁዳ ነገድ የይፉኔ ልጅ ካሌብ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰዎቹም ስም ይህ ነው፤ ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፥ |
ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ በዚህም ጊዜ “እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።
ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ በእርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርስዋ አስቀምጣችሁ ዘንድ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም።
እግዚአብሔር ስለ እነርሱ፥ “በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ” ብሎ ተናግሮአልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ፥ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው ስንኳ አልቀረም።
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በስተቀር፥ እርሱ ግን ያያታል፤ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱ፥ ለልጆቹም እሰጣለሁ።
የይሁዳም በረከት ይህች ናት፤ አቤቱ የይሁዳን ቃል ስማ፤ ወደ ሕዝቡም ይግባ፤ እጆቹም ይግዙ፤ በጠላቶቹ ላይ ረዳት ትሆነዋለህ።