Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 14:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከ​ተ​ለኝ እርሱ ወደ ገባ​ባት ምድር አገ​ባ​ዋ​ለሁ፤ ዘሩም ይወ​ር​ሳ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 አገልጋዬ ካሌብ ግን የተለየ መንፈስ ስላለውና በፍጹም ልቡ የተከተለኝ በመሆኑ ሄዶባት ወደ ነበረችው ምድር አስገባዋለሁ፤ ዘሮቹም ይወርሷታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ባርያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለ ተከተለኝ እርሱ ሄዶ ወደ ነበረበት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ነገር ግን አገልጋዬ ካሌብ ልዩ አመለካከት ስላለውና ለእኔ ያለውንም ታማኝነት ስላጸና ሄዶ የመረመራትን ምድር እሰጠዋለሁ፤ ዘሮቹም ያቺን ምድር ይወርሳሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ባሪያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 14:24
17 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርጉ እንደ ክር​ስ​ቶስ ባሮች እንጂ ለሰው ደስ እን​ደ​ሚ​ያ​ሰኝ ለታ​ይታ አይ​ደ​ለም።


በደ​ረሰ ጊዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸን​ተው ይኖሩ ዘንድ መከ​ራ​ቸው።


ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ በስ​ተ​ቀር፥ እርሱ ግን ያያ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ተከ​ት​ሎ​አ​ልና የረ​ገ​ጣ​ትን ምድር ለእ​ርሱ፥ ለል​ጆ​ቹም እሰ​ጣ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ፥ “በእ​ው​ነት በም​ድረ በዳ ይሞ​ታሉ” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ፥ ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ስንኳ አል​ቀ​ረም።


ካሌ​ብም ሕዝ​ቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰ​ኘና፥ “አይ​ደ​ለም! ማሸ​ነ​ፍን እን​ች​ላ​ለ​ንና እን​ውጣ፤ እን​ው​ረ​ሳት” አለ።


ለሰው ሳይ​ሆን ለጌታ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ርጉ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ከልብ አድ​ር​ጉት።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልብ አይ​ደ​ለም።


አቤቱ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ሆይ፥ ይህን አሳብ በሕ​ዝ​ብህ ልብ ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብቅ፤ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ አንተ አቅና።


ሕዝ​ቡም ፈቅ​ደው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፥ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቅ​ር​በ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ፥ በፍ​ጹ​ምም ኀይ​ልህ ውደድ።


ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይጠብቁ።


ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር በእ​ር​ስዋ አስ​ቀ​ም​ጣ​ችሁ ዘንድ እጄን ዘር​ግቼ ወደ ማል​ሁ​ላ​ችሁ ምድር በእ​ው​ነት እና​ንተ አት​ገ​ቡም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios