Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 26:65 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

65 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ፥ “በእ​ው​ነት በም​ድረ በዳ ይሞ​ታሉ” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ፥ ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ስንኳ አል​ቀ​ረም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

65 ምክንያቱም በርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ነግሯቸው ነበር፤ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

65 ጌታ ስለ እነርሱ፦ “በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ” ብሎ ተናግሮአልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ አልቀረም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

65 ይህም የሆነው “ሁሉም በምድረ በዳ ይሞታሉ!” ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ ስለ ነበር ነው፤ ስለዚህም ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ሁሉም ሞተዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

65 እግዚአብሔር ስለ እነርሱ፦ በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ ብሎ ተናግሮአልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው ስንኳ አልቀረም።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 26:65
20 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ምድ​ሪ​ቱን ሊሰ​ልሉ ከሄዱ ሰዎች የነዌ ልጅ ኢያ​ሱና የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ በሕ​ይ​ወት ኖሩ።


እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርኅ​ራ​ኄ​ው​ንና ጭካ​ኔ​ውን አስ​ተ​ውል፤ የወ​ደ​ቁ​ትን ቀጣ​ቸው፤ አን​ተን ግን ይቅር እን​ዳ​ለህ ብት​ኖር ማረህ፤ ያለ​ዚያ ግን አን​ተም ትቈ​ረ​ጣ​ለህ።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በእኔ ላይ በተ​ሰ​በ​ሰበ በዚህ ክፉ ማኅ​በር ሁሉ ላይ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያል​ቃሉ፤ በዚ​ያም ይሞ​ታሉ።”


ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


የእ​ና​ንተ ግን በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ።


“አባ​ታ​ችን በም​ድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢ​አት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገን መካ​ከል አል​ነ​በ​ረም፤ ወን​ዶ​ችም ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም።


የሰ​ዎ​ቹም ስም ይህ ነው፤ ከይ​ሁዳ ነገድ የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ፥


ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ በስ​ተ​ቀር፥ እርሱ ግን ያያ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ተከ​ት​ሎ​አ​ልና የረ​ገ​ጣ​ትን ምድር ለእ​ርሱ፥ ለል​ጆ​ቹም እሰ​ጣ​ለሁ።


ኢያሱ ሕዝ​ቡን ሁሉ የገ​ረ​ዘ​በት ምክ​ን​ያት ይህ ነው፤ ከግ​ብፅ የወጡ ወን​ዶች ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ ላይ በም​ድረ በዳ ሞቱ፤ የወ​ጡ​ትም ወን​ዶች ሁሉ ተገ​ር​ዘው ነበር።


አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊ​ትህ ነው፥ ጩኸ​ቴም ከአ​ንተ አይ​ሰ​ወ​ርም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios