ዘዳግም 33:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 የይሁዳም በረከት ይህች ናት፤ አቤቱ የይሁዳን ቃል ስማ፤ ወደ ሕዝቡም ይግባ፤ እጆቹም ይግዙ፤ በጠላቶቹ ላይ ረዳት ትሆነዋለህ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ስለ ይሁዳ የተናገረው ይህ ነው፦ “እግዚአብሔር ሆይ፤ የይሁዳን ጩኸት ስማ፤ ወደ ወገኖቹም አምጣው። በገዛ እጆቹ ራሱን ይከላከላል፤ አቤቱ ከጠላቶቹ ጋራ ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ስለ ይሁዳም እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ፥ የይሁዳን ድምፅ ስማ፥ ወደ ወገኖቹም አምጣው። እጆቹንም አጠንክርለት፤ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋም ረዳት ሁነው።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ስለ ይሁዳ ነገድም እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ የይሁዳን ነገድ ጩኸት ስማ፤ ከሌሎች ነገዶች ጋር እንዲተባበር አድርግ፤ የበረታ ኀይል ስጣቸው፤ ከጠላቶቻቸው ጋር በሚዋጉበት ጊዜ ርዳቸው።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 የይሁዳ በረከት ይህ ነው፤ እንዲህም አለ፦ 2 አቤቱ፥ የይሁዳን ድምፅ ስማ፥ 2 ወደ ወገኖቹም አግባው፤ 2 እጆቹ ይጠንክሩለት፤ 2 በጠላቶቹ ላይ ረዳት ትሆነዋለህ። Ver Capítulo |