ሮብዓምም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሠራ፤ አባቶቹ በሠሩት ኀጢአትና በደል ሁሉ እንደ አስቀኑት በሠራው ኀጢአት አስቀናው።
ዘዳግም 32:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በጣዖቶቻቸውም አስቈጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በከንቱ ጣዖቶቻቸው አስቈጡኝ። እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በሞኝ ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በምናምንቴዎቻቸውም አስቆጡኝ፥ እኔም በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፥ በማያስተውል ሕዝብ አስቆጣቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነተኛ ባልሆኑ አማልክት አስቀንተውኛል፤ ዋጋቢስ በሆኑ ጣዖቶቻቸው አስቈጥተውኛል፤ በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ ቍ 15 በዕብራይስጥ ይሹሩን የሚለውን ግዕዙ ያዕቆብ ይለዋል። 2 በምናምንቴዎቻቸውም አስቈጡኝ፤ 2 እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ 2 በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ። |
ሮብዓምም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሠራ፤ አባቶቹ በሠሩት ኀጢአትና በደል ሁሉ እንደ አስቀኑት በሠራው ኀጢአት አስቀናው።
ከአንተም አስቀድመው ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስቈጣኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎችን አማልክትና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎች አደረግህ፤ ወደ ኋላህም ተውኸኝ።
ባኦስና ልጁ ኤላ ስለ ሠሩት ኀጢአት ሁሉ፥ በርኵሰታቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያስቈጡት ዘንድ እስራኤልን ስለ አሳቱበት ኀጢአት፥ ዘምሪ የባኦስን ቤት ሁሉ እንዲሁ አጠፋ።
በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ ሁሉ በርኩስነታቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያስቈጡት ዘንድ እስራኤልን ባሳተበት ኀጢአት ሄደ።
እግዚአብሔርም ከፊታቸው ያወጣቸው አሕዛብ እንዳደረጉት፥ በኮረብቶቹ መስገጃዎች ሁሉ ላይ ያጥኑ ነበር፤ እግዚአብሔርንም ያስቈጡ ዘንድ የማምለኪያ ዐፀዶችንና ሐውልቶችን አደረጉ፤
የገባላቸውንም ቃል ኪዳን ሁሉ አልጠበቁም። ከንቱ ነገርንም ተከተሉ፤ ከንቱም ሆኑ፤ እንደ እነርሱም እንዳይሠሩ ያዘዛቸውን በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ።
ልጁንም በእሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ በእግዚአብሔርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ፤ ኣስቈጣውም።
በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ታስቈጡኝ ዘንድ ትታችሁኛልና፥ ለሌሎች አማልክትም ዐጥናችኋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።
በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰጥና ሊያጠግብ ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።
ሕዝቤ ግን ረስተውኛል፤ ለከንቱ ነገርም አጥነዋል፤ የቀድሞውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማማውና ወደ ሰንከልካላው መንገድ ለመሄድ በመንገዳቸው ተሰናከሉ።
አሕዛብ አማልክት ያልሆኑ አማልክቶቻቸውን ይለውጡ አንደ ሆነ እዩ፤ ነገር ግን ሕዝቤ ክብራቸውን ለማይረባ ነገር ለወጡ።
“ከእነዚህ ነገሮች በየትኛው ይቅር እልሻለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፤ አጠገብኋቸውም፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ በአመንዝራዎቹም ቤት ዐደሩ።
ያስቈጡኝ ዘንድ፥ ለሰማይ ንግሥት እንጎቻ እንዲያደርጉ፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፤ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ።
እነሆ እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የወገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተቀረፁ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱነትስ ያስቈጡኝ ስለ ምንድን ነው?
እጅ መሳይንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕሬም ያዘኝ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፤ በእግዚአብሔርም ራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ ቅንአት የተባለው ምስል ወደ አለበት አመጣኝ፤
የእስራኤልም ልጆች ቍጥር እንደማይሰፈርና እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እንዲህም ይሆናል፤ “እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም” ተብሎ በተነገረበት በዚያ ስፍራ የሕያው አምላክ ልጆች ይባላሉ።
እንዲህም አሉአቸው፥ “እናንተ ሰዎች፥ ይህን ነገር ለምን ታደርጋላችሁ? እኛስ እንደ እናንተ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን? ነገር ግን ይህን ከንቱ ነገር ትታችሁ ሰማይና ምድርን፥ ባሕርንም በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እናስተምራችኋለን።
እስራኤል ብቻ አልሰሙምን? ሙሴስ አስቀድሞ እንዲህ ብሎአቸው የለምን? “እኔ በማያስተውሉ ወገኖች አስቀናቸዋለሁ፤ ወገን ባልሆነውም አስቈጣቸዋለሁ።”
ነቢዩ ሆሴዕ እንዲህ እንዳለ “ወገኔ ያልነበረውን ወገኔ አደርገዋለሁ፤ ወዳጄ ያልነበረችውንም ወዳጄ አደርጋታለሁ።
ለእግዚአብሔር ያይደለ ለአጋንንት፥ ለማያውቋቸውም አማልክት፥ ድንገት ለተገኙ ለማይሠሩና ለማይጠቅሙ አማልክት፥ አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው አማልክት ሠዉ።