Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 32:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በዚህ በልዩ ጣዖት አነ​ሣ​ሡኝ፤ በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም አስ​መ​ረ​ሩኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፤ በአስጸያፊ ጣዖቶቻቸውም አስቈጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፥ በርኩሰታቸውም አስቆጡት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔርን በጣዖት አምልኮ አስቀኑት፤ በሚያደርጉትም ክፉ ነገር ሁሉ አስቈጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በሌሎች አማልክት አስቀኑት፥ 2 በርኩሰታቸውም አስቈጡት።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 32:16
20 Referencias Cruzadas  

እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​ስ​ቀ​ና​ውን? በውኑ እኛ ከእ​ርሱ እን​በ​ረ​ታ​ለን?


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ፊት ለፊት በር​ኵ​ስት ተራራ ቀኝ የነ​በ​ሩ​ትን፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለሲ​ዶ​ና​ው​ያን ርኵ​ስት ለአ​ስ​ታ​ሮት፥ ለሞ​ዓ​ብም ርኵ​ሰት ለካ​ሞሽ፥ ለአ​ሞ​ንም ልጆች ርኵ​ሰት ለሞ​ሎክ ያሠ​ራ​ቸ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ንጉሡ ርኩስ አደ​ረገ።


ሮብ​ዓ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሠራ፤ አባ​ቶቹ በሠ​ሩት ኀጢ​አ​ትና በደል ሁሉ እንደ አስ​ቀ​ኑት በሠ​ራው ኀጢ​አት አስ​ቀ​ናው።


የአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ምስል በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠ​ራ​ባ​ቸ​ውን ብር​ንና ወር​ቅን፥ አት​መኝ፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እን​ዳ​ት​በ​ድ​ል​በት ከእ​ርሱ ምንም አት​ው​ሰድ።


አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና፤ በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና እስከ አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤


ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በ​ሩት የሀ​ገሩ ልጆች ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ታ​ልና፤


አም​ላክ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ኑኝ፤ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አስ​ቈ​ጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝ​ብም አስ​ቈ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ዐውሎ ነፋ​ሱ​ንም ጸጥ አደ​ረገ፥ ባሕ​ሩም ዝም አለ።


ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አድ​ኜ​ማ​ለሁ፤ መክ​ሬ​ማ​ለሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ ባዕድ አም​ልኮ አል​ነ​በ​ረም፤ ስለ​ዚህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እንደ ሆንሁ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ፤


እግ​ር​ሽን ከሰ​ን​ከ​ል​ካላ መን​ገድ፥ ጕሮ​ሮ​ሽ​ንም ከውኃ ጥም ከል​ክዪ፤ እር​ስዋ ግን፥ “እጨ​ክ​ና​ለሁ፤ እን​ግ​ዶ​ች​ንም ወድ​ጄ​አ​ለሁ” ብላ ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።


ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እን​ጎቻ እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን እን​ዲ​ያ​ፈ​ስሱ ልጆች እን​ጨት ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ አባ​ቶ​ችም እሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ ሴቶ​ችም ዱቄት ይለ​ው​ሳሉ።


እጅ መሳ​ይ​ንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕ​ሬም ያዘኝ፤ መን​ፈ​ስም በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራእይ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ በር መግ​ቢያ ቅን​አት የተ​ባ​ለው ምስል ወደ አለ​በት አመ​ጣኝ፤


ከአ​ን​ተም አስ​ቀ​ድ​መው ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስ​ቈ​ጣ​ኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን ምስ​ሎች አደ​ረ​ግህ፤ ወደ ኋላ​ህም ተው​ኸኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው ያወ​ጣ​ቸው አሕ​ዛብ እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት፥ በኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ሁሉ ላይ ያጥኑ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንና ሐው​ል​ቶ​ችን አደ​ረጉ፤


ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ሥዉ​አ​ቸው፤ ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም ሆኑ፤ ያስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር ለማ​ድ​ረግ ራሳ​ቸ​ውን ሸጡ።


ልጁ​ንም በእ​ሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ኣስ​ቈ​ጣ​ውም።


አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ያል​ሆኑ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይለ​ውጡ አንደ ሆነ እዩ፤ ነገር ግን ሕዝቤ ክብ​ራ​ቸ​ውን ለማ​ይ​ረባ ነገር ለወጡ።


እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን የለ​ምን? ወይስ ንጉ​ሥዋ በእ​ር​ስዋ ዘንድ የለ​ምን? የሚል የወ​ገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተ​ቀ​ረፁ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውና በባ​ዕድ ከን​ቱ​ነ​ትስ ያስ​ቈ​ጡኝ ስለ ምን​ድን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios