“ሕዝብህም ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትመልሳቸው መንገድ ቢወጡ፥ አንተም ወደ መረጥሃት ከተማ፥ እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤት በእግዚአብሔር ስም ቢጸልዩ፥
2 ዜና መዋዕል 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳም፥ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም” ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ደካሞችን ከኀይለኞች የሚታደግ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ታምነናልና፣ ይህን ታላቅ ሰራዊት በስምህ እንገጥመዋለን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳም እንዲህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ ጌታ ጮኸ፦ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህምና፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ! በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፥ ኀያላኑንም ሠራዊት ሆነ ደካማውንም የመርዳት ችሎታ አለህ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ በአንተ ስለ ተማመንን እነሆ፥ ይህን ብዙ ሠራዊት ለመውጋት መጥተናልና እባክህ እርዳን፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ አምላካችን ነህ፤ አንተን ማሸነፍ የሚችል ማንም የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳም “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህምና፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ! በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና፥ እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ” ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። |
“ሕዝብህም ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትመልሳቸው መንገድ ቢወጡ፥ አንተም ወደ መረጥሃት ከተማ፥ እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤት በእግዚአብሔር ስም ቢጸልዩ፥
በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና በእርሱም ታምነዋልና አዳናቸው፤ በላያቸውም በረቱባቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ።
እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኻሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አቷጉ።”
የይሁዳም ሰዎች ወደ ኋላቸው በተመለከቱ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰልፉ በፊታቸውና በኋላቸው ነበረ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከቱን ነፉ።
የይሁዳም ሰዎች ጮኹ፤ የይሁዳም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እግዚአብሔር ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በይሁዳ ንጉሥ በአብያና በሕዝቡ ፊት መታቸው።
በዚያም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ተዋረዱ፤ የይሁዳም ልጆች በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ነበርና አሸነፉ።
በዚያን ጊዜም ነቢዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “በሶርያ ንጉሥ ታምነሃልና፥ በአምላክህም በእግዚአብሔር አልታመንህምና ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ ጭፍራ ከእጆችህ አምልጠዋል።
የሰረገሎችም አለቆች ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእስራኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋጠሙትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፤ እግዚአብሔርም አዳነው፤ አምላኩም ከእርሱ መለሳቸው።
አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን መቃወም እንችል ዘንድ ኀይል የለንም፤ የምናደርግባቸውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።”
ብትሄድ ግን፥ በእነርሱም ማሸነፍን ብታስብ፥ የማጽናትና የመጣል ኀይል ከእግዚአብሔር ዘንድ ነውና እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት ይጥልሃል” አለው።
ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳን የሚዋጋልንም አምላካችን እግዚአብሔር ነው።” ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና።
በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፥ በሚያሠቃዩኝ ሰዎች፤ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋህም የተትረፈረፈ ነው፥ ያረካልም።
ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዐይናቸውን አነሡ፤ እነሆም፥ ግብፃውያን ሲከተሉአቸው አዩ፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
በዚያም ጊዜ እንዲህ ይሆናል፤ የእስራኤል ቅሬታ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት ከእንግዲህ ወዲህ በአቈሰሉአቸው ላይ አይደገፉም፤ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ።
ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፤ መቶውም ዐሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም፤ ልባችሁ አይደንግጥ፤ አትፍሩም።
ስሙን በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፤ እርሱንም በማመን በፊታችሁ ይህን ሕይወት ሰጠው።
ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።
አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ስለ አገልጋዮቹም ይራራል፤ በያሉበት መሳለቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይላቸውም እንደ ደከመ፥ በጠላትም እጅ እንደ ወደቁ አይቶአልና።
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፥ “በእጃቸው ውኃ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያምንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ የቀሩት ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍራቸው ይመለሱ” አለው።
ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ሰፈር እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል” አለው።
ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደለ ያውቃል። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፤ እግዚአብሔርም እናንተን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።”