Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 5:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ​ዋ​ልና በእ​ር​ሱም ታም​ነ​ዋ​ልና አዳ​ና​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም በረ​ቱ​ባ​ቸው፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከእ​ነ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተሰጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በጦርነቱም ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው ስለ ነበር፣ በውጊያው ረዳቸው፤ አጋራውያንንና የጦር አጋሮቻቸውን ሁሉ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ስለ ታመኑበትም ጸሎታቸውን ሰማ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ እነርሱንም ረዳቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተላልፈው ተሰጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እምነታቸውንም በእግዚአብሔር አድርገው እርሱ እንዲረዳቸው ተማጠኑት፤ እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ፥ በሀጋራውያንና በእነርሱም የጦር ጓደኞች ላይ ድልን አጐናጸፋቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ በላያቸውም ረዳት ሆናቸው፤ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 5:20
35 Referencias Cruzadas  

ይስ​ሐ​ቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ፤ መካን ነበ​ረ​ችና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብ​ቃም ፀነ​ሰች።


“ጋድን ሽፍ​ቶች ቀሙት፤ እር​ሱም ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ታ​ትሎ ቀማ​ቸው።


የሰ​ረ​ገ​ሎች አለ​ቆ​ችም የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “በእ​ው​ነት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ይመ​ስ​ላል፤” አሉ ይዋ​ጉ​ትም ዘንድ ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ጮኸ።


ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አምሳ ሺህ ግመ​ሎች፥ ሁለት መቶ አምሳ ሺህም በጎች፥ ሁለት ሺህም አህ​ዮች፥ ከሰ​ዎ​ችም መቶ ሺህ ማረኩ።


ሰልፉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ረና ብዙ ሰዎች ተገ​ድ​ለው ወደቁ፤ እስከ ምር​ኮም ዘመን ድረስ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።


በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተዋ​ረዱ፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታም​ነው ነበ​ርና አሸ​ነፉ።


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም አለ​ቆች ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋ​ጠ​ሙ​ትም ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነው፤ አም​ላ​ኩም ከእ​ርሱ መለ​ሳ​ቸው።


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ አት​ፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ው​ምን? ይህን የመ​ጣ​ብ​ንን ታላቅ ወገን መቃ​ወም እን​ችል ዘንድ ኀይል የለ​ንም፤ የም​ና​ደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ው​ንም አና​ው​ቅም፤ ነገር ግን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ወደ አንተ ናቸው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በዓ​ለት ላይ በሚ​ኖሩ ዓረ​ባ​ው​ያን፥ በም​ዕ​ዑ​ና​ው​ያ​ንም ላይ አጸ​ናው።


የን​ጉሡ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምና​ሴም ጸለየ እን​ዲ​ህም አለ፦


ስለ​ዚ​ህም ነገር ጾምን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ንን፤ እር​ሱ​ም​ሰ​ማን።


አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ እጆ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ብ​ጭቡ፥ በደ​ስታ ቃልም ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ።


ስም​ህን የሚ​ወዱ ሁሉ በአ​ንተ ይታ​መ​ናሉ፥ አቤቱ፥ የሚ​ሹ​ህን አት​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምና።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአ​ነሣ ጊዜ እስ​ራ​ኤል ድል ያደ​ርግ ነበር ፤ እጁ​ንም በአ​ወ​ረደ ጊዜ ዐማ​ሌቅ ድል ያደ​ርግ ነበር።


ፈጽሜ አድ​ን​ሃ​ለሁ፤ ሰው​ነ​ት​ህም እንደ ምርኮ ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች እንጂ በሰ​ይፍ አት​ወ​ድ​ቅም፤ በእኔ ታም​ነ​ሃ​ልና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።


ይኸ​ውም አስ​ቀ​ድ​መን በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ ተስፋ ያደ​ረ​ግን እኛ ለክ​ብሩ ምስ​ጋና እን​ሆን ዘንድ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ይዋጋ ነበ​ርና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ውን ቃል የሰ​ማ​በት እን​ደ​ዚያ ያለ ቀን ከዚ​ያም በፊት ከዚ​ያም በኋላ አል​ነ​በ​ረም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተዋ​ጋ​ላ​ቸው ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ንድ ጊዜ ያዘ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረን ስለ እና​ንተ የሚ​ዋጋ እርሱ ነውና ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳ​ድ​ዳል።


ሳኦ​ልም፥ “እገ​ድ​ለው ዘንድ ዳዊ​ትን ከነ​አ​ል​ጋው” አም​ጡ​ልኝ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹን ወደ ዳዊት ላከ።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos