መዝሙር 22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የዳዊት መዝሙር። 1 እግዚአብሔር ይጠብቀኛል፥ የሚያሳጣኝም የለም። 2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ አሳደገኝ። 3 ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። 4 በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል። 5 በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፥ በሚያሠቃዩኝ ሰዎች፤ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋህም የተትረፈረፈ ነው፥ ያረካልም። 6 ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተለኝ፤ በእግዚአብሔር ቤት ለረዥም ዘመን እኖር ዘንድ። |