መዝሙር 145:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላኬና ንጉሤ ሆይ! ታላቅነትህን ዐውጃለሁ፤ ለዘለዓለምም አመሰግንሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት የምስጋና መዝሙር። አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም እባርካለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች። |
ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፤ በደመናዎች ላይ ለሚጓዘው መንገድ አዘጋጁ፤ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤ በፊቱ ደስ ይበላችሁ!
እግዚአብሔር ያድነኛል፤ ስለዚህ እኛ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ አውታር ባለው የሙዚቃ መሣሪያ የምሥጋና መዝሙር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዘምራለን።
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።
በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!