መዝሙር 100 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምየምስጋና መዝሙር 1 በምድር ላይ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር “እልል!” በሉ! 2 እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት! የደስታ መዝሙር እየዘመራችሁ ወደ እርሱ ፊት ቅረቡ! 3 እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ የፈጠረን እርሱ ነው፤ እኛ የእርሱ ነን፤ ስለዚህ እኛ እንደ በጎች መንጋ የሚያሰማራን ሕዝቦቹ ነን። 4 እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤ ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ። 5 እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩና ታማኝነቱ ዘለዓለማዊ ነው። |