የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ማስታወቂያዎች


ንዑስ ምድብ

116 የፍቅር የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋዎች

ፍቅር ማለት ከቃላት ይልቅ በተግባር የሚገለጽ ስሜት ነው።

እንዴት እንደሚወደን አስቡት፤ ኢየሱስ ስለ እያንዳንዳችን ኃጢአት ይቅርታ እንዲሆንልን ራሱን አሳልፎ ሰጠ። ይህ የፍቅር ጥልቅ ማሳያ ነው። ኢየሱስ ፍቅሩን በቃላት ሳይሆን በዝምታ፣ እኔና አንተ በክፋታችን የሚገባንን ጅራፍ በመቀበል አሳየን።

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ምሳሌ የለም። የእርሱን የፍቅር መንገድ መከተል ከሁሉም በላይ ዋጋ ያለው ነገር ነው። እግዚአብሔር እርሱ እንደወደደን እኛም እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ይፈልጋል።

እውነተኛ ፍቅር የሚመነጨው ከማያልቀው ምንጭ ከእግዚአብሔር ነው። ይህንን ፍቅር አንዴ ከተቀበልክ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መውደድን ትማራለህ።

እግዚአብሔር በፍቅር የሚራመድ እና ለችግረኞች ሁሉንም ነገር ለመስጠት የተዘጋጀ ትውልድ እንዲፈጠር ይሻል። ይህ ዓለም ፍቅር የጎደለው ነው፣ አንተ ደግሞ በምድር ላይ የኢየሱስ ነጸብራቅ እንድትሆን ተጠርተሃል።

ፍቅር ከቀለምና ከማህበራዊ ደረጃ በላይ ነው። ሌሎች ምን ሊሰጡህ እንደሚችሉ ሳይሆን አንተ ለሌሎች ምን ያህል መስጠት እንደምትችል ነው። ፍቅር በዚህ ላይ የተመሠረተ ነው።


1 ቆሮንቶስ 16:14

የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ።

1 ዮሐንስ 4:19

እርሱ አስቀድሞ ወድዶናልና እኛ እንወድደዋለን።

ሮሜ 5:8

ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል።

ምሳሌ 21:21

ጽድቅንና ፍቅርን የሚከተል፤ ሕይወትን ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።

1 ቆሮንቶስ 13:4-7

ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤

ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም።

ፍቅር ከእውነት ጋራ እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም።

ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል።

መዝሙር 136:26

የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

ዮሐንስ 3:16

በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና።

ገላትያ 5:22-23

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣

ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው። እንደነዚህ ያሉትንም የሚከለክል ሕግ የለም።

ኤፌሶን 2:4-5

ነገር ግን በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ፣

በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው።

መዝሙር 145:8

እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ፣ ለቍጣ የዘገየ፣ ታማኝነቱም የበዛ ነው።

ቈላስይስ 3:14

በእነዚህ ሁሉ ላይ ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት።

ምሳሌ 3:3-4

ፍቅርና ታማኝነት ከቶ አይለዩህ፤ በዐንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤ በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው።

ምንም ጕዳት ሳያደርስብህ፣ ያለ ምክንያት ሰውን አትክሰስ።

በክፉ ሰው አትቅና፤ የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ።

እግዚአብሔር ጠማማን ሁሉ ይጸየፋልና፤ ለቅን ሰው ግን ምስጢሩን ይገልጥለታል።

የእግዚአብሔር ርግማን በክፉዎች ቤት ላይ ነው፤ የጻድቃንን ቤት ግን ይባርካል።

እርሱ በዕቡያን ፌዘኞች ላይ ያፌዛል፤ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል።

ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፤ ሞኞችን ግን ለውርደት ያጋልጣቸዋል።

በዚያ ጊዜ ሞገስንና ማስተዋልን፣ በእግዚአብሔርና በሰው ዘንድ ታገኛለህ።

1 ዮሐንስ 4:16

ስለዚህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ በፍቅሩም እናምናለን። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል።

1 ቆሮንቶስ 13:13

እንግዲህ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።

ማቴዎስ 22:37-39

እርሱም እንዲህ አለው፤ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤’

ይህ የመጀመሪያውና ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ ነው፤

ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል፤ ይህም፣ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’ የሚለው ነው፤

ኤፌሶን 4:2

ፍጹም ትሑታንና ገሮች ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁም በፍቅር እየተቻቻላችሁ ትዕግሥተኞች ሁኑ።

ኤፌሶን 5:2

ክርስቶስ እንደ ወደደን ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ተመላለሱ።

1 ጴጥሮስ 4:8

ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና፣ ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤

መዝሙር 86:15

ጌታ ሆይ፤ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ ለቍጣ የዘገየህ፣ ምሕረትህና ታማኝነትህ የበዛ።

ሮሜ 12:9

ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፤ ክፉ የሆነውን ሁሉ ተጸየፉ፤ በጎ ከሆነው ነገር ጋራ ተቈራኙ።

ሮሜ 8:38-39

ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣ መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣ ያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣

ከፍታም ይሁን ጥልቀት ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።

ዮሐንስ 15:12

ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።

ማቴዎስ 5:44

እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ፤

1 ቆሮንቶስ 13:2

የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ ምስጢርን ሁሉና ዕውቀትን ሁሉ ባውቅ፣ ተራራንም ከቦታው የሚነቅል እምነት ቢኖረኝ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።

2 ተሰሎንቄ 3:15

ሆኖም እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።

ገላትያ 6:2

አንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህም ሁኔታ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።

ሮሜ 12:10

እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ።

ኢሳይያስ 54:10

ተራሮች ቢናወጡ፣ ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤ የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም” ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።

1 ዮሐንስ 4:12

እግዚአብሔርን ያየ ከቶ ማንም የለም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ ግን እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፤ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።

1 ዮሐንስ 4:20

ማንም፣ “እግዚአብሔርን እወድደዋለሁ” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፣ እርሱ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና።

መዝሙር 143:8

በአንተ ታምኛለሁና፣ በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና፣ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።

ዕብራውያን 13:1

እርስ በርሳችሁ እንደ ወንድማማች ተዋደዱ።

ዮሐንስ 15:13

ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ማንም የለውም፤

1 ዮሐንስ 4:18

በፍቅር ፍርሀት የለም፤ ፍጹም ፍቅር ግን ፍርሀትን አውጥቶ ይጥላል፤ ፍርሀት ከቅጣት ጋራ የተያያዘ ነውና። የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።

1 ተሰሎንቄ 3:12

እኛ ለእናንተ ፍቅር እንዳለን ሁሉ እርስ በርስ ያላችሁን ፍቅርና ለሌሎችም ያላችሁን ፍቅር ጌታ ያብዛላችሁ፤ ያትረፍርፍላችሁም።

ሮሜ 5:5

ይህም ተስፋ ለዕፍረት አይዳርገንም፤ እግዚአብሔር በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን አፍስሷልና።

መዝሙር 136:1

እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

ምሳሌ 10:12

ጥላቻ ጠብን ያነሣሣል፤ ፍቅር ግን ስሕተትን ሁሉ ይሸፍናል።

1 ጴጥሮስ 1:22

እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን ስላነጻችሁ፣ ለወንድሞቻችሁ ቅን ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ።

ሰቈቃወ 3:22-23

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።

ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህም ብዙ ነው።

መዝሙር 118:1

እግዚአብሔር ቸር ነውና አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

ማቴዎስ 12:30

“ከእኔ ጋራ ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔም ጋራ የማይሰበስብ ይበትናል።

ይሁዳ 1:2

ምሕረት፣ ሰላምና ፍቅር ይብዛላችሁ።

ቈላስይስ 2:2

ደግሞም ልባቸው እንዲጽናናና በፍቅር እንዲተሳሰሩ፣ ፍጹም የሆነውን የመረዳት ብልጽግና አግኝተው የእግዚአብሔር ምስጢር የሆነውን ክርስቶስን እንዲያውቁ እተጋለሁ፤

ሮሜ 13:10

ፍቅር በባልንጀራው ላይ ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ መፈጸሚያ ነው።

ማቴዎስ 7:12

ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና።

ሮሜ 8:35

ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ችግር ነው ወይስ ሥቃይ፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ራብ፣ ወይስ ዕራቍትነት፣ ወይስ አደጋ፣ ወይስ ሰይፍ?

1 ዮሐንስ 4:10

ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው።

መዝሙር 103:8

እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ፣ ለቍጣ የዘገየ፣ ታማኝነቱም የበዛ ነው።

መዝሙር 42:8

እግዚአብሔር ምሕረቱን በቀን ያዝዛል፤ ዝማሬውም በሌሊት በእኔ ዘንድ አለ፤ ይህም ለሕይወቴ አምላክ የማቀርበው ጸሎት ነው።

1 ቆሮንቶስ 8:3

እግዚአብሔርን የሚወድድ ሰው ግን በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።

1 ዮሐንስ 2:15

ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድድ የአብ ፍቅር በርሱ ዘንድ የለም፤

ኢሳይያስ 63:9

በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ፤ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በምሕረቱ ዋጃቸው፤ በቀደመው ዘመን ሁሉ አነሣቸው፤ ተሸከማቸውም።

መዝሙር 86:5

ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም።

1 ዮሐንስ 5:3

እግዚአብሔርን መውደድ ትእዛዞቹን መፈጸም ነውና። ትእዛዞቹም ከባድ አይደሉም፤

ገላትያ 5:14

ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ተጠቃሏል፤ ይኸውም፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚል ነው።

መዝሙር 136:4

እርሱ ብቻውን ታላላቅ ታምራትን የሚያደርግ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

ኤፌሶን 1:4-5

በፊቱ ቅዱስና እንከን አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በርሱ መርጦናልና። በፍቅር፣

በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤

2 ቆሮንቶስ 5:14

የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ ርግጠኞች ሆነናል፣ ከዚህም የተነሣ ሁሉ ሞተዋል።

ሮሜ 14:15

ወንድምህ በምትበላው ምግብ የሚያዝን ከሆነ፣ በፍቅር አልተመላለስህም፤ ክርስቶስ የሞተለትን ወንድምህን በመብልህ አታጥፋው።

መዝሙር 37:4

በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።

ፊልጵስዩስ 2:1-2

ከክርስቶስ ጋራ ካላችሁ አንድነት የተነሣ የትኛውም መበረታታት፣ ከፍቅር የሆነ መጽናናት፣ የመንፈስ ኅብረት፣ ምሕረትና ርኅራኄ ካላችሁ፣

ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች፣ ጕልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣

ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፤ ሁልጊዜም ታዛዦች እንደ ነበራችሁ ሁሉ፣ አሁንም እኔ በአጠገባችሁ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፣ ይልቁንም አሁን በሌለሁበት ጊዜ በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

እንደ በጎ ፈቃዱ መፈለግንና ማድረግን በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።

ማንኛውንም ነገር ሳታጕረመርሙና ሳትከራከሩ አድርጉ፤

ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው።

የሕይወትንም ቃል ስታቀርቡ፣ በከንቱ እንዳልሮጥሁ ወይም በከንቱ እንዳልደከምሁ በክርስቶስ ቀን የምመካበት ይሆንልኛል።

ነገር ግን በእምነታችሁ መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ እንደ መጠጥ ቍርባን ብፈስስ እንኳ ከሁላችሁ ጋራ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ።

እናንተም እንደዚሁ ከእኔ ጋራ ደስ ልትሠኙና ሐሤት ልታደርጉ ይገባል።

ስለ እናንተ ሰምቼ ደስ እንዲለኝ፣ ጢሞቴዎስን ቶሎ ወደ እናንተ ልልክላችሁ በጌታ ኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።

በአንድ ሐሳብ፣ በአንድ ፍቅር፣ በአንድ መንፈስና በአንድ ዐላማ በመሆን ደስታዬን ፍጹም አድርጉልኝ።

ምሳሌ 17:17

ወዳጅ ምን ጊዜም ወዳጅ ነው፤ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል።

መዝሙር 100:5

እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።

ኢሳይያስ 49:15

“እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም!

መዝሙር 138:2

ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤ ስምህንና ቃልህን፣ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

ቈላስይስ 3:12-14

እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደ መሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤

እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ።

በእነዚህ ሁሉ ላይ ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት።

1 ቆሮንቶስ 13:1-3

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ።

ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ በከፊል የነበረው ይሻራል።

ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ ዐስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላ ነበር። ከጐለመስሁ በኋላ ግን የልጅነትን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ።

አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያ ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያ ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።

እንግዲህ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።

የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ ምስጢርን ሁሉና ዕውቀትን ሁሉ ባውቅ፣ ተራራንም ከቦታው የሚነቅል እምነት ቢኖረኝ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።

ያለኝን ሁሉ ለድኾች ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ለእሳት ብዳርግ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

ዕብራውያን 10:24-25

እርስ በርሳችንም ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ።

አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ።

መዝሙር 136:5

ሰማያትን በብልኀት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

ማቴዎስ 22:39

ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል፤ ይህም፣ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’ የሚለው ነው፤

ኤፌሶን 3:17-19

ይኸውም በእምነት ክርስቶስ በልባችሁ እንዲያድር ነው። ደግሞም ሥር ሰድዳችሁ፣ በፍቅር ታንጻችሁ፣

የክርስቶስ ፍቅር ስፋቱ፣ ርዝመቱ፣ ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ፣ ከቅዱሳን ሁሉ ጋራ የመገንዘብ ኀይልን እንድታገኙ ነው።

እስከ እግዚአብሔር ሙላት ሁሉ ልክ ደርሳችሁ እንድትሞሉ፣ ከመታወቅ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር ታውቁም ዘንድ ነው።

ገላትያ 5:6

በክርስቶስ ኢየሱስ ከሆኑ፣ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና፤ የሚጠቅመውስ በፍቅር የሚገለጽ እምነት ብቻ ነው።

1 ጴጥሮስ 4:8-9

ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና፣ ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤

እርስ በርሳችሁ ያለ ማጕረምረም እንግድነት ተቀባበሉ።

1 ቆሮንቶስ 13:8

ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል።

ሮሜ 8:31

ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል?

መዝሙር 86:12

ጌታ አምላኬ ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ፤

ኢሳይያስ 43:4

ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣ እኔም ስለምወድድህ፣ ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ።

ማቴዎስ 5:16

እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።

ሮሜ 1:11-12

እንድትጸኑ የሚያስችላችሁን መንፈሳዊ ስጦታ አካፍላችሁ ዘንድ፣ ላያችሁ እናፍቃለሁ።

ይኸውም እናንተና እኔ በእያንዳንዳችን እምነት እርስ በርሳችን እንድንበረታታ ነው።

2 ቆሮንቶስ 13:11

በተረፈ ወንድሞች ሆይ፤ ደኅና ሁኑ፤ ፍጹማን ሁኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ አንድ ሐሳብ ይኑራችሁ፤ በሰላምም ኑሩ። የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋራ ይሆናል።

ኤፌሶን 5:25

ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳትና ራሱንም ስለ እርሷ አሳልፎ እንደ ሰጠ፣ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤

መዝሙር 78:38

እርሱ ግን መሓሪ እንደ መሆኑ፣ በደላቸውን ይቅር አለ፤ አላጠፋቸውም፤ ቍጣውን ብዙ ጊዜ ገታ፤ መዓቱንም ሁሉ አላወረደም።

1 ዮሐንስ 2:5

ነገር ግን ማንም ቃሉን ቢጠብቅ፣ በእውነት የእግዚአብሔር ፍቅር በርሱ ፍጹም ሆኗል። በርሱ መሆናችንን የምናውቀው በዚህ ነው፤

መዝሙር 119:64

እግዚአብሔር ሆይ፤ ምድር በምሕረትህ ተሞላች፤ ሥርዐትህን አስተምረኝ።

1 ጴጥሮስ 2:17

ለሰው ሁሉ ተገቢውን አክብሮት ስጡ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።

ሮሜ 15:30

ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የተጋድሎዬ አጋር እንድትሆኑ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ፍቅር እለምናችኋለሁ።

ዕብራውያን 13:2

እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ፣ ሳያውቁ መላእክትን አስተናግደዋልና።

መዝሙር 37:21

ኀጢአተኛ ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ ጻድቅ ግን ይቸራል።

መዝሙር 116:1-2

የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት።

“እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣ እምነቴን ጠብቄአለሁ።

ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።

ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?

የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።

የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።

እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤ እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፤ ከእስራቴም ፈታኸኝ።

ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።

በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤

ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ። ሃሌ ሉያ።

ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።

1 ዮሐንስ 3:16-18

ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ ስለ ሰጠ፣ ፍቅር ምን እንደ ሆነ በዚህ እናውቃለን፤ እኛም ሕይወታችንን ስለ ወንድሞቻችን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባናል።

ማንም የዚህ ዓለም ሀብት እያለው፣ ወንድሙ ሲቸገር አይቶ ልቡ ባይራራለት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት በርሱ ይኖራል?

ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።

መዝሙር 56:3-4

ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣ መታመኔን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።

ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

ገላትያ 2:20

ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው።

መዝሙር 131:2

ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሠኘኋት፤ ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች።

ምሳሌ 19:17

ለድኻ የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ ስላደረገውም ተግባር ዋጋ ይከፍለዋል።

ኢሳይያስ 41:13

እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና አትፍራ ይልሃል፤ እረዳሃለሁ።

1 ቆሮንቶስ 13:5

ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም።

መዝሙር 89:1

ስለ እግዚአብሔር ምሕረት ለዘላለም እዘምራለሁ፤ በአፌም ታማኝነትህን ከትውልድ እስከ ትውልድ እገልጻለሁ።

መዝሙር 91:14

“ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ።

ሮሜ 15:5

ብርታትንና መጽናናትን የሚሰጥ አምላክ፣ ክርስቶስ ኢየሱስን ስትከተሉ፣ በመካከላችሁ አንድ ሐሳብ ይስጣችሁ፤

1 ዮሐንስ 4:21

እርሱም “እግዚአብሔርን የሚወድድ ሁሉ ወንድሙን መውደድ ይገባዋል” የሚለውን ይህን ትእዛዝ ሰጥቶናል።

መዝሙር 119:159

መመሪያህን እንዴት እንደምወድድ ተመልከት፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ።

ገላትያ 6:7-9

አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል።

ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን።

2 ተሰሎንቄ 3:5

ጌታ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ወደ ክርስቶስ ጽናት ይምራው።

ዕብራውያን 10:23

የተስፋን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለ ሆነ፣ አምነን የምንናገርለትን ተስፋ አጥብቀን እንያዝ።

መዝሙር 119:165

ሕግህን የሚወድዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤ ዕንቅፋትም የለባቸውም።

መዝሙር 31:23

እናንተ ቅዱሳኑ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ውደዱት! እግዚአብሔር ታማኞችን ይጠብቃል፤ ትዕቢተኞችን ግን ፈጽሞ ይበቀላቸዋል።

ምሳሌ 15:16-17

እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋራ ያለ ጥቂት ነገር፣ ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል።

ፍቅር ባለበት ጐመን መብላት፣ ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይሻላል።

ሮሜ 13:8

እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር የማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤ ባልንጀራውን የሚወድድ እርሱ ሕግን ፈጽሟልና።

1 ቆሮንቶስ 13:4-8

ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤

ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም።

ፍቅር ከእውነት ጋራ እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም።

ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል።

ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል።

2 ተሰሎንቄ 2:16-17

ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ደግሞም እኛን የወደደንና በጸጋው የዘላለም መጽናናትና መልካም ተስፋን የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን፣

ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎ ሥራና በቃል ሁሉ ያበርቷችሁ።

1 ዮሐንስ 3:1

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ልጆቹ ነን። ዓለም እኛን የማያውቀንም እርሱን ስላላወቀው ነው።

1 ዮሐንስ 4:7

ወዳጆች ሆይ፤ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል።

1 ዮሐንስ 4:8

የማይወድድ ግን እግዚአብሔርን አያውቅም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚኦ አባቴ ሆይ፤ አንተ ብቻ ይገባሃል፤ ክብርና ምስጋና ሁሉ ላንተ ይሁን። በኃያል በኢየሱስ ስም እጸልያለሁ፤ ባለፈው ጊዜ ሁሉ ጋሻዬና መጠጊያዬ ስለነበርክ አመሰግንሃለሁ። ወዳጄ አምላክ ሆይ፤ ሌሎችን በአንተ ዓይን እንዳያቸውና በአንተ ልብ እንዳፈቅራቸው እርዳኝ። የሰዎችን ችግር ተረድቼ፤ በተቻለኝ መጠን እንዳግዛቸው፤ ጆሮዬንና ልቤን ክፈትልኝ። ለድሀ፣ ለወላጅ ለሌለው ልጅና ለባልቴት፤ እጄን ለመዘርጋት የልግስና መንፈስ ስጠኝ። መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በሆነ መንገድ የጎዱኝን ሁሉ ይቅር እንዳላቸው፤ እርዳኝ። ከእነሱ ጋር ስገናኝ፤ በልቤ ምሬትና ቂት እንዳይኖር፤ ልቤን ፈውስልኝ። ቃልህ «ከነዚህ ከታናናሾቹ ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁትን ለእኔ አደረጋችሁት» ይላል። እንደ ኢየሱስህ ሌሎችን እንዳገለግል እርዳኝ፤ የኃይልህና የክብርህ ተሸካሚ እንድሆን፤ ያለኝን በአግባቡ ተጠቅሜ እንደ አንተ ፈቃድ ለሚያስፈልጋቸው እንዳካፍል እርዳኝ። ከቤተሰቦቼ፣ ከወዳጆቼና ከባልደረቦቼ ጋር መልካም፤ የሚያንጽና የሚያፈራ ግንኙነት እንዲኖረኝ ጥበብን ስጠኝ። ፍቅር የፍጹም ማሰሪያ ስለሆነ፤ አምላኬ ሆይ፤ ልቤን በፍቅር ሞላው። በኢየሱስ ስም፤ አሜን።