እግዚአብሔር ስለ አንቺ ሲያስብ፣ ታማኝ፣ ደፋር እና እውነተኛ ጓደኛ፣ መታመን የሚቻልባት፣ ታታሪ እና ተጋዳይ፣ በማንኛውም ሁኔታ የማትወድቅ፣ እውነተኛ ማንነቷን የምትኖር፣ በማዕበል ውስጥም እንኳን የምትጨፍር፣ በብርድ መጠጊያ፣ በሙቀት ደግሞ ነፍስን የሚያድስ እስትንፋስ የሆነች አጋር አድርጎ አስቦ ነበር።
አንቺ የፍቅር መገለጫ ነሽ። ትልቅ ልብ፣ የመስጠት ባህሪ እና የተትረፈረፈ እምነት አለሽ። ለዚህም ነው በኢየሱስ ስም ታላላቅ ጦርነቶችን የምታሸንፊው።
ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ አንቺ ወሳኝ ሚና ተጫውተሻል። በአንቺ በኩል ሕይወት ይፈልቃል። በድፍረትሽ እና በድጋፍሽ አዲስ ፍጥረት ወደዚህ ዓለም ይመጣል። ምንም ዓይነት ሕመም ሊያስቆምሽ አይችልም። ብቸኛው ጠላትሽ የራስሽ አስተሳሰብ ብቻ ነው።
እግዚአብሔር ሙሉ አድርጎ ስለፈጠረሽ፣ ዲያብሎስ ሁልጊዜ ሊያጠቃሽ እና ሊያስቆምሽ ይፈልጋል። ስለዚህ በመልካም ነገሮች ላይ አስቢ።
ደፋር እና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተሰጠሽ ነሽ። ለእግዚአብሔር እና ለወገኖችሽ ባደረግሽው አገልግሎት ከሰማይ ዋጋ እንደምታገኚ እመኚ። የምታደርጊው ምንም ነገር በከንቱ አይሆንም። አባት ሥራሽን ያያል እና በጊዜው በሰዎች ፊት ያከብርሻል።
ስለዚህ መልካም ማድረግን አትተዪ። የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድ ለማድረግ ጠብቂ እና ከቃሉ አትራቂ። በእግዚአብሔር እና በተስፋዎቹ እመኚ። የተስፋ ቃሉ ፍጻሜ ቢዘገይም እንኳን ልብ በይ፤ እግዚአብሔር የገባልሽን ለመፈጸም አይዘገይም።
ቤተሰብሽ፣ ልጆችሽ እና ባልሽ በኢየሱስ እጅ ናቸው። ስለወደፊትሽ አትፍሪ። በየማለዳ የሚያነሳሽ የጸጋው ኃይል ያበረታሽ።
አሁን ልጄ ሆይ፣ አትፍሪ። የምትለምኚኝን ሁሉ አደርግልሻለሁ። ሕዝቤ ሁሉ አንቺ ምሳሌ የሚሆን ሴት እንደሆንሽ ያውቃል። (ሩት 3:11)
ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንቍ እጅግ ትበልጣለች። ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤ የሚጐድልበትም ነገር የለም። በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣ መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም። የበግ ጠጕርና የተልባ እግር መርጣ፣ ሥራ በሚወድዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች። እንደ ንግድ መርከብ፣ ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች። ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች። ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤ በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች። ብርታትን ታጥቃ ሥራዋን ታከናውናለች፤ ክንዶቿም ለሥራ ብርቱ ናቸው። ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤ በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም። በእጇ እንዝርት ትይዛለች፤ በጣቶቿም ዘንጉን ታሾራለች። “ልጄ ሆይ፤ የማሕፀኔ ልጅ ሆይ፤ የስእለቴ ልጅ ሆይ፤ ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣ እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች። በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤ ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና። ለመኝታዋ የዐልጋ ልብስ ትሠራለች፤ ቀጭን በፍታና ሐምራዊ ልብስ ለብሳለች። ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከል በአደባባይ በተቀመጠ ጊዜ የተከበረ ነው። የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች። ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤ መጪውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች። በጥበብ ትናገራለች፤ በአንደበቷም ቀና ምክር አለ። የቤተ ሰቦቿን ጕዳይ በትጋት ትከታተላለች፤ የስንፍና እንጀራ አትበላም። ልጆቿ ተነሥተው ቡርክት ይሏታል፤ ባሏም እንዲሁ፣ ሲያመሰግናትም እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ሴቶች መልካም አድርገዋል፤ አንቺ ግን ሁሉንም ትበልጫለሽ።” ጕልበትህን በሴት አትጨርስ፤ ብርታትህንም ነገሥታትን ለሚያጠፉ አታውል። ቍንጅና አታላይ ነው፤ ውበትም ይረግፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን የተመሰገነች ናት። የሚገባትን ሽልማት ስጧት፤ ሥራዋም በየአደባባዩ ያስመስግናት።
ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምን ጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን፤
ሚስቶች ሆይ፤ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ፣ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና።
ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ! ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው፤ ጠጕርሽም ከገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፣ የፍየል መንጋ ነው።
እርሱ ግን፣ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ ፍጹም የሚሆነው በድካም ጊዜ ነውና” አለኝ። ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ያድር ዘንድ፣ ይበልጥ ደስ እያለኝ በድካሜ እመካለሁ።
ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን፣ ይኸውም፣ ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን፤ ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምን ጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን፤
እንዲህ ከሆኑ፣ ወጣት ሴቶች ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወድዱ ማስተማር ይችላሉ፤ የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤ ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና የምታደርግ አንተ ነህ። ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፤ እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ
በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤ የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።
ሚስቶች ሆይ፤ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ፣ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና። እንግዲህ ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ፣ ሚስቶችም ለባሎቻቸው በማንኛውም ነገር እንደዚሁ መገዛት ይገባቸዋል።
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው። እንደነዚህ ያሉትንም የሚከለክል ሕግ የለም።
የግብጽም ንጉሥ ሲፓራና ፉሐ የተባሉትን ዕብራውያን ሴቶች አዋላጆች እንዲህ አላቸው፤ “የዕብራውያንን ሴቶች በማማጫው ድንጋይ ላይ በምታዋልዱበት ጊዜ የሚወለደው ሕፃን ወንድ ከሆነ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።” አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ የግብጽ ንጉሥ ያዘዛቸውን አልፈጸሙም፤ ወንዶቹንም ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ተዉአቸው። ንጉሡም አዋላጆቹን ጠርቶ፣ “ለምንድን ነው ወንዶቹን ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ የተዋችኋቸው?” አላቸው። እነርሱም፣ “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብጻውያን ሴቶች አይደሉም፤ ብርቱዎች ስለ ሆኑ አዋላጆች ከመድረሳቸው በፊት ይወልዳሉ” ሲሉ ለፈርዖን መለሱለት። ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለአዋላጆቹ መልካም ሆነላቸው፤ ሕዝቡም በቍጥር እየበዛና እያየለ ሄደ።
ሩት ግን እንዲህ አለች፤ “ተለይቼሽ እንድቀር ወይም እንድመለስ አትለማመጭኝ፤ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምትኖሪበትም እኖራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል። በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ እዚያው እቀበራለሁ። ከእንግዲህ ሞት ከሚለየን በቀር ብለይሽ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ ከዚህም የከፋ ያድርግብኝ።”
እንዲሁም አሮጊቶች በአኗኗራቸው የተከበሩ እንዲሆኑ፣ በጎ የሆነውን የሚያስተምሩ እንጂ የሰው ስም የሚያጠፉ ወይም በወይን ጠጅ ሱስ የተጠመዱ እንዳይሆኑ አስተምራቸው።
የሰውየው ስም ናባል፣ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር።
እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሣራን ዐሰባት፤ የገባውንም ተስፋ ፈጸመላት። አብርሃምንም፣ “ይህችን ባሪያ ከነልጇ አባርራት፤ የዚህች ባሪያ ልጅ፣ ከልጄ ከይሥሐቅ ጋራ አይወርስምና” አለችው። እስማኤል ልጁ ስለ ሆነ ነገሩ አብርሃምን እጅግ አስጨነቀው። እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ስለ ልጁም ሆነ ስለ አገልጋይህ ሐሳብ አይግባህ፤ ዘር የሚጠራልህ በይሥሐቅ በኩል ስለ ሆነ፣ ሣራ የምትልህን ሁሉ ስማ። የአገልጋይህም ልጅ የራስህ ልጅ ስለ ሆነ፣ እርሱንም ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ።” በማግስቱም አብርሃም ማልዶ ተነሣ። ጥቂት ምግብ ወስዶ፣ ውሃ በእርኮት አድርጎ ለአጋር ሰጣት፤ በትከሻዋም አሸክሟት ከነልጇ አሰናበታት። እርሷም ሄደች፤ በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ትንከራተት ጀመር። በእርኮት የነበረው ውሃ ባለቀ ጊዜ፣ ልጁን ከአንድ ቍጥቋጦ ሥር አስቀመጠችው። ከዚያም፣ “ልጁ ሲሞት ዐይኔ አያይም” ብላ፣ የቀስት ውርወራ ያህል ርቃ ዐረፍ አለች፤ እርሷም እየተንሰቀሰቀች ታለቅስ ጀመር። እግዚአብሔርም የልጁን ጩኸት ሰማ። የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ አላት፤ “አጋር ሆይ፤ ምን ሆነሻል? ልጅሽ ከተኛበት ሲያለቅስ እግዚአብሔር ሰምቶታል፤ ስለዚህ አትፍሪ። ተነሥተሽ ልጁን አንሺው፤ ያዢውም፤ ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁና።” እግዚአብሔርም ዐይኖቿን ከፈተላት፤ የውሃ ጕድጓድም አየች፤ ሄዳም በእርኮቱ ውሃ ሞልታ ልጇን አጠጣች። ሣራ ፀነሰች፤ ልክ እግዚአብሔር ባለው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት።
በእስራኤል ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዷ እኔ ነኝ፤ አንተ በእስራኤል እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት ትሻለህ፤ የእግዚአብሔርን ርስት ለመዋጥ የፈለግኸው ለምንድን ነው?”
ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች። ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤ በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች።
ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣ የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣ ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ።
በክንክራኦስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነችውን እኅታችንን ፌቤንን ዐደራ እላችኋለሁ። በክርስቶስ ያለው እምነቱ ተፈትኖ ለተመሰገነው ለኤጤሌን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከአርስጣባሉ ቤተ ሰብ ለሆኑትም ሰላምታ አቅርቡልኝ። ለዘመዴ ለሄሮድዮና ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ ላሉት ለንርቀሱ ቤተ ሰቦች ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ ሆነው በትጋት ለሚሠሩት ሴቶች፣ ለፕሮፊሞናና ለጢሮፊሞሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ ሆና እጅግ ለደከመችው ለሌላዋ ሴት፣ ለተወደደችው ለጠርሲዳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ ለተመረጠው ለሩፎንና የእኔም እናት ለሆነችው ለእናቱ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ፣ ለሄሮሜን፣ ለጳጥሮባን፣ ለሄርማን፣ ከእነርሱም ጋራ ላሉት ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ። ለፍሌጎን፣ ለዩልያ፣ ለኔርያና ለእኅቱ፣ እንዲሁም ለአልንጦን፣ ከእነርሱም ጋራ ላሉት ቅዱሳን ሰላምታ አቅርቡልኝ። በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ። የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። ወንድሞች ሆይ፤ መለያየትን ከሚፈጥሩትና የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም በጕዟችሁ መሰናክል ከሚያደርጉት እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ። እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የሚያገለግሉት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ሆድ ነው። በለሰለሰ አንደበታቸውና በሽንገላ የዋሆችን ያታልላሉ። የእናንተን ታዛዥነት ሁሉም ሰምተዋል፤ በዚህም እኔ እጅግ ተደስቻለሁ። ሆኖም በጎ ስለ ሆነው ነገር ጥበበኞች፣ ክፉ ስለ ሆነውም የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። ለቅዱሳን ተገቢ በሆነው አቀባበል በጌታ እንድትቀበሏትና ከእናንተም የምትፈልገውን ማንኛውንም ርዳታ እንድታደርጉላት አሳስባችኋለሁ፤ ለብዙ ሰዎችና ለእኔም ጭምር ታላቅ ድጋፍ ነበረችና።
አዎን፤ አንተ ታማኝ ባልደረባዬ ሆይ፤ ወንጌልን በማሠራጨት ረገድ ከእኔና ከቀሌምንጦስ ጋራ እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ጓደኞቼ ጋራ የተጋደሉትን እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ።
ራሔልም አባቷን፣ “በፊትህ ተነሥቼ መቆም ስላልቻልሁ፣ ጌታዬ አትቈጣ፤ የወር አበባዬ መጥቶ ነው።” አለችው፤ ስለዚህ በረበረ፤ የጣዖታቱን ምስል ግን ማግኘት አልቻለም።
የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።
ልጆችን በማሳደግ፣ እንግዶችን በመቀበል፣ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና ለበጎ ምግባር ሁሉ ራሷን በመስጠት በመልካም ሥራም የተመሰከረላት መሆን አለባት።
ባሎች ሆይ፤ እናንተም ደግሞ ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ በኑሯችሁ ሁሉ ለሚስቶቻችሁ ዐስቡላቸው፤ ደካሞች ስለ ሆኑና የሕይወትንም በረከት ዐብረዋችሁ ስለሚወርሱ አክብሯቸው።
መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።
ብዙ መከራና ጭንቅ ብታሳየኝም፣ ሕይወቴን እንደ ገና ታድሳለህ፤ ከምድር ጥልቅም፣ እንደ ገና ታወጣኛለህ። ክብሬን ትጨምራለህ፤ ተመልሰህም ታጽናናኛለህ።
ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንቍ እጅግ ትበልጣለች። ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤ የሚጐድልበትም ነገር የለም። በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣ መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም።