መዝሙር 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልባችን ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን፥ ከዘይትም ይልቅ በዛ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስንዴና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ባመረቱ ጊዜ ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ፣ አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። አቤቱ፥ የፊትህን ብርሃን በላያችን አንሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች ከእህልና ከወይን ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ አንተ በልቤ ያኖርከው ደስታ ይበልጣል። |
ከወደ ኋላህም ሳቡህ፥ በሽቱህ መዓዛም እንሮጣለን፤ ንጉሡ ወደ እልፍኙ አገባኝ፤ በአንቺ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ጡቶችሽን እንወዳለን፤ አንቺንም መውደድ የተገባ ነው።
ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞአብ ምድር ጠፍተዋል፤ ወይን ከመጥመቂያው ጠፍቶአል፤ በነግህ የሚጠምቁት የለም፤ በሠርክም የሚያደርጉት የእልልታ ድምፅ የለም።
ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራን እየሠራ ከሰማይ ዝናምን፥ ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።”
እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
ወደ እርሻውም ወጡ፤ ወይናቸውንም ለቀሙ፤ ጠመቁትም፤ የደስታም በዓል አደረጉ፤ ወደ አምላካቸውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤሜሌክንም ረገሙት።