Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 48:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ሐሤ​ትና ደስታ ከፍ​ሬ​ያ​ማው እር​ሻና ከሞ​አብ ምድር ጠፍ​ተ​ዋል፤ ወይን ከመ​ጥ​መ​ቂ​ያው ጠፍ​ቶ​አል፤ በነ​ግህ የሚ​ጠ​ም​ቁት የለም፤ በሠ​ር​ክም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉት የእ​ል​ልታ ድምፅ የለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ከሞዓብ የአትክልት ቦታና ዕርሻ፣ ሐሤትና ደስታ ርቋል፤ የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤ በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤ በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣ የእልልታ ድምፅ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፤ የወይ ጠጁን ከወይን መጥመቂያው አጥፍቻለሁ፤ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ደስታና ሐሴት ለምለም ከሆነችው ከሞአብ ምድር ተወስደዋል፤ ከወይን መጭመቂያዎች ሁሉ የወይን ጠጅ እንዳይፈስስ አድርጌአለሁ፤ የደስታ ድምፅ እያሰማ የሚጨምቅ የለም፤ ድምፅ የሚሰማ ቢሆንም የሚሰማው ድምፅ ግን የደስታ ድምፅ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፥ ጠጁን ከመጥመቂያው አጥፍቻለሁ፥ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 48:33
13 Referencias Cruzadas  

ዐሥር ጥማድ በሬ ካረ​ሰው የወ​ይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወ​ጣል፤ ስድ​ስት መስ​ፈ​ሪያ የዘራ ሦስት መሥ​ፈ​ሪያ ብቻ ያገ​ባል።


በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ወይን በሀ​ገሩ ሁሉ የበጀ ይሆ​ናል፤ የአ​ንድ ሺህ የወ​ይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆ​ናል። ከዚህ በኋላ ዳግ​መኛ ምድር ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ት​ንም ትሞ​ላ​ለች፤ ፍር​ሀ​ትም ይመ​ጣል።


ብዙ ሕዝ​ብን በደ​ስታ አወ​ረ​ድህ፤ በመ​ከር ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው፥ ምር​ኮ​ንም እን​ደ​ሚ​ካ​ፈሉ በፊ​ትህ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ከዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችሁ ፊት ምግብ፥ ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ቤት ደስ​ታና ሐሤት ጠፍ​ቶ​አል።


እና​ንተ ሰካ​ራ​ሞች፥ ንቁ፤ ለመ​ስ​ከ​ርም ወይ​ንን የም​ት​ጠጡ እና​ንተ ሁላ​ችሁ! ተድ​ላና ደስታ ከአ​ፋ​ችሁ ጠፍ​ት​ዋ​ልና አል​ቅሱ፤ እዘ​ኑም።


በመ​ካ​ከ​ልህ አል​ፋ​ለ​ሁና በጎ​ዳ​ናው ሁሉ ልቅሶ ይሆ​ናል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በዚያን ዘመን ሁሉ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፣ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው ሀያ ብቻ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos