Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “በጎ​ውን ማን ያሳ​የ​ናል?” የሚሉ ብዙ​ዎች ናቸው። አቤቱ፥ የፊ​ትህ ብር​ሃን በላ​ያ​ችን ታወቀ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል?” ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በጌታም ታመኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “መልካሙን ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ! የፊትህ ብርሃን በእኛ ላይ ይብራ!

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 4:6
20 Referencias Cruzadas  

እኔ ግን ትል ነኝ፥ ሰውም አይ​ደ​ለ​ሁም፤ በሰው ዘንድ የተ​ና​ቅሁ፥ በሕ​ዝ​ብም ዘንድ የተ​ዋ​ረ​ድሁ ነኝ።


መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ ሥጋ​ህን አን​ጻ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና ስለ ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አል​ወ​ደ​ድ​ሁም።


ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝ​ኛ​ለሽ? ለም​ንስ ታው​ኪ​ኛ​ለሽ? የፊ​ቴን መድ​ኀ​ኒት አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኚ።


ኀያል ሆይ፥ በደም ግባ​ት​ህና በው​በ​ትህ፥ ሰይ​ፍ​ህን በወ​ገ​ብህ ታጠቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይነሣ፥ ጠላ​ቶ​ቹም ይበ​ተኑ፥ የሚ​ጠ​ሉ​ትም ከፊቱ ይሽሹ።


በመ​ከ​ራህ ጊዜ ጠራ​ኸኝ፥ አዳ​ን​ሁ​ህም፥ በተ​ሰ​ወረ ዐው​ሎም መለ​ስ​ሁ​ልህ፥ በክ​ር​ክር ውኃ ዘን​ድም ፈተ​ን​ሁህ።


መከ​ራን ባሳ​የ​ኸን ዘመን ፋንታ፥ ክፉ​ንም ባየ​ን​ባት ዘመን ፋንታ ደስ ይለ​ናል።


ገን​ዘ​ብን እን​ጀራ ላይ​ደለ፥ የድ​ካ​ማ​ች​ሁ​ንም ዋጋ ለማ​ያ​ጠ​ግብ ነገር ለምን ትመ​ዝ​ና​ላ​ችሁ? አድ​ም​ጡኝ፤ በረ​ከ​ት​ንም ብሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ደስ ይበ​ለው።


እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፣ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላ​ም​ንም ይስ​ጥህ።


ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዲህ እላ​ታ​ለሁ፦ ሰው​ነቴ ሆይ፥ የሰ​በ​ሰ​ብ​ሁ​ልሽ ለብዙ ዓመ​ታት የሚ​በ​ቃሽ የደ​ለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበ​ልሽ።


“አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅ​ግም ቀጭን ልብስ ይለ​ብስ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ተድ​ላና ደስታ ያደ​ርግ ነበር።


አሕ​ዛ​ብን ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ያም ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ የጽ​ድቅ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ይሠ​ዋሉ፤ የባ​ሕ​ሩም ሀብት፥ በባ​ሕሩ ዳር የሚ​ኖሩ ሰዎ​ችም ገን​ዘብ ይመ​ግ​ብ​ሃ​ልና፥


አሁንም “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን፤ በዚያም ዓመት እንኖራለን፤ እንነግድማለን፤ እናተርፍማለን፤” የምትሉ እናንተ! ተመልከቱ፤ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos