Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


በእግዚአብሔር መታመን

1 ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።

2 የጽድቄ አምላክ ሆይ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፥ በጭንቀቴም አሰፋህልኝ፥ ማረኝ፥ ጸሎቴንም ስማ።

3 እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ታዋርዳላችሁ? ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?

4 በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፥ ጌታ ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።

5 ፍሩ፥ ኃጢአትንም አትሥሩ፥ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ አስቡ፥ ዝምም በሉ።

6 የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በጌታም ታመኑ።

7 በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። አቤቱ፥ የፊትህን ብርሃን በላያችን አንሣ።

8 በልቤ ደስታን ጨመርህ፥ ከስንዴ ፍሬያቸውና ከወይናቸው ይልቅ በዛ።

9 በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፥ አቤቱ፥ አንተ ብቻ በደኅንነት ታሳድረኛለህና።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos