Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘኍል 6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የና​ዝ​ራ​ው​ያን ሕግ

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

2 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ያደ​ርግ ዘንድ ልዩ ስእ​ለት ቢሳል፥

3 ከወ​ይን ጠጅና ከሚ​ያ​ሰ​ክር መጠጥ ራሱን የተ​ለየ ያድ​ርግ፤ ከወ​ይን ወይም ከሌላ ከሚ​ያ​ሰ​ክር ነገር የሚ​ገ​ኘ​ውን ሆም​ጣጤ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም ጭማቂ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም እሸት ወይም ዘቢብ አይ​ብላ።

4 ራሱን የተ​ለየ ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ከወ​ይን የሆ​ነ​ውን ነገር ሁሉ ከው​ስጡ ፍሬ ጀምሮ እስከ ደረ​ቀው ዘቢብ ድረስ አይ​ብላ።

5 “ራሱን ለመ​ለ​የት ስእ​ለት ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ራሱን አይ​ላጭ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለ​የ​በት ወራት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ቅዱስ ይሆ​ናል፤ የራ​ሱ​ንም ጠጕር ያሳ​ድ​ጋል።

6 “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይ​ቅ​ረብ።

7 ለአ​ም​ላኩ ያደ​ረ​ገው ብፅ​ዐት በራሱ ላይ ነውና አባቱ፥ ወይም እናቱ፥ ወይም ወን​ድሙ፥ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰው​ነ​ቱን አያ​ር​ክ​ስ​ባ​ቸው።

8 በብ​ፅ​ዐቱ ወራት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ነውና።

9 “ሰውም በአ​ጠ​ገቡ ድን​ገት ቢሞት የራሱ ብፅ​ዐት ይረ​ክ​ሳል፤ እርሱ በሚ​ነ​ጻ​በት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ይላ​ጨው።

10 በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ያምጣ፤

11 ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ በሬ​ሳም የተ​ነሣ ኀጢ​አት ሠር​ቶ​አ​ልና ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ በዚ​ያም ቀን ራሱን ይቀ​ድ​ሰ​ዋል።

12 በስ​እ​ለቱ ወራ​ትም ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቀ​ደ​ሳል፤ የአ​ንድ ዓመ​ትም ተባት ጠቦት ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያምጣ፤ ስእ​ለቱ ግን ረክ​ሶ​አ​ልና ያለ​ፈው ወራት ሁሉ አይ​ቈ​ጠ​ር​ለ​ትም።

13 “የተ​ሳ​ለው ሰው ሕግ ይህ ነው፤ የስ​እ​ለቱ ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ ራሱ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ይቅ​ረብ፤ ቍር​ባ​ኑ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቅ​ርብ።

14 ነውር የሌ​ለ​በት የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ትን የአ​ንድ ዓመት እን​ስት ጠቦት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አውራ በግ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት፥

15 አንድ ሌማ​ትም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የስ​ንዴ ቂጣ እን​ጀራ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን ያቅ​ርብ።

16 ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቅ​ር​በው። የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ያሳ​ር​ግ​ለ​ታል።

17 አው​ራ​ው​ንም በግ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከሌ​ማቱ ቂጣ እን​ጀራ ጋር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ደግሞ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የመ​ጠ​ጡን ቍር​ባን ያቀ​ር​ባል።

18 የተ​ሳ​ለ​ውም የተ​ሳ​ለ​ውን የራስ ጠጕር በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን አጠ​ገብ ይላ​ጫል፤ የስ​እ​ለ​ቱ​ንም ራስ ጠጕር ወስዶ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በታች ወዳ​ለው እሳት ይጥ​ለ​ዋል።

19 ካህ​ኑም የተ​ቀ​ቀ​ለ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ወርች፥ ከሌ​ማ​ቱም አንድ ቂጣ እን​ጎቻ፥ አን​ድም ስስ ቂጣ ይወ​ስ​ዳል፤ የተ​ሳ​ለ​ው​ንም የራስ ጠጕር ከተ​ላጨ በኋላ በባ​ለ​ስ​እ​ለቱ እጆች ላይ ያኖ​ራ​ቸ​ዋል።

20 ካህ​ኑም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ቍር​ባን አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​ባል፤ ይህም የቍ​ር​ባን ፍር​ም​ባና የመ​ባው ወርች ለካ​ህኑ የተ​ቀ​ደሰ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ባለ​ስ​እ​ለቱ ወይን ይጠ​ጣል።

21 “ስእ​ለ​ቱን የተ​ሳ​ለው የባ​ለ​ስ​እ​ለቱ፥ እጁም ከሚ​ያ​ገ​ኘው ሌላ ስለ ስእ​ለቱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በው የቍ​ር​ባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእ​ለ​ቱን እንደ ተሳለ እንደ ስእ​ለቱ ሕግ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።”


የካ​ህ​ናት ቡራኬ

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

23 “ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ንገ​ራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስት​ባ​ር​ኩ​አ​ቸው እን​ዲህ በሉ​አ​ቸው፦

24 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ፥ ይጠ​ብ​ቅ​ህም፤

25 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊቱን ያብ​ራ​ልህ፥ ይራ​ራ​ል​ህም።

26 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላ​ም​ንም ይስ​ጥህ።

27 እን​ዲሁ ስሜን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ይጠ​ራሉ፤ እኔም እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos