Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 9:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ወደ እር​ሻ​ውም ወጡ፤ ወይ​ና​ቸ​ው​ንም ለቀሙ፤ ጠመ​ቁ​ትም፤ የደ​ስ​ታም በዓል አደ​ረጉ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ረገ​ሙት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ወደ ዕርሻ ወጥተው ወይናቸውን ለቅመው ከጨመቁ በኋላ በአምላካቸው ቤት የደስታ በዓል አደረጉ፤ በዚያም እየበሉና እየጠጡ አቢሜሌክን ሰደቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ወደ ዕርሻ ወጥተው ወይናቸውን ለቅመው ከጨመቁ በኋላ በአምላካቸው ቤት የደስታ በዓል አደረጉ፤ በዚያም እየበሉና እየጠጡ አቤሜሌክን ሰደቡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ሁሉም ወደ ወይን ተክሎቻቸው ወጥተው የወይን ፍሬ ለቀሙ፤ የወይን ጠጅ ጠምቀው ትልቅ በዓል አደረጉ፤ ወደ አምላካቸውም መቅደስ ገብተው በዚያ እየበሉና እየጠጡ ስለ አቤሜሌክ በማፌዝ ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ወደ እርሻውም ወጡ ወይናቸውንም ለቀሙ፥ ጠመቁትም፥ የደስታም በዓል አደረጉ፥ ወደ አምላካቸውም ቤት ገቡ፥ በሉም ጠጡም፥ አቤሜሌክንም ሰደቡ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 9:27
20 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀ​ርብ ጥጃ​ው​ንም ዘፈ​ኑ​ንም አየ፤ የሙ​ሴም ቍጣ ተቃ​ጠለ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለ​ቱን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተ​ራ​ራው በታች ሰበ​ራ​ቸው።


አሮ​ንም በነ​ጋው ማልዶ ተነሣ፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ሠዋ፤ የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ ሕዝ​ቡም ሊበ​ሉና ሊጠጡ ተቀ​መጡ፤ ሊዘ​ፍ​ኑም ተነሡ።


“ስለ​ዚ​ህም ይህን ቃል ሁሉ ትን​ቢት ትና​ገ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ ሆኖ እንደ አን​በሳ ያገ​ሣል፤ በቅ​ዱስ ማደ​ሪ​ያ​ውም ሆኖ ድም​ፁን ያሰ​ማል፤ በበ​ረቱ ላይ እጅግ ያገ​ሣል፤ ወይ​ንም እን​ደ​ሚ​ጠ​ምቁ በም​ድር በሚ​ኖሩ ሁሉ ላይ ይጮ​ኻል።


በመ​ኝ​ታ​ቸው ላይ ሆነው ያለ​ቅሱ ነበር እንጂ በል​ባ​ቸው ወደ እኔ አል​ጮ​ኹም፤ ስለ እህ​ልና ስለ ወይን ይገ​ዳ​ደሉ ነበር፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ቱም ሴት ልጅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠርቶ ሰደበ፤ ወደ ሙሴም አመ​ጡት። እና​ቱም ከዳን ነገድ የዳ​ቤር ልጅ ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ሰሎ​ሚት ነበረ።


የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መሳ​ፍ​ን​ትም፥ “አም​ላ​ካ​ችን ጠላ​ታ​ች​ንን ሶም​ሶ​ንን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን” እያሉ ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ለዳ​ጎን ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት ይሠዉ ዘንድ፥ ደስም ይላ​ቸው ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ጌዴ​ዎን ከሞተ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ በዓ​ሊ​ም​ንም ተከ​ት​ለው አመ​ነ​ዘሩ፤ በዓ​ሊ​ምም አም​ላክ ይሆ​ና​ቸው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ።


የአ​ቤ​ድም ልጅ ገዓል ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር መጣ፤ የሰ​ቂማ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ተባ​በሩ።


ከበ​ዓ​ልም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፤ በዚ​ያም አቤ​ሜ​ሌክ ወን​በ​ዴ​ዎ​ች​ንና አስ​ደ​ን​ጋ​ጮ​ችን ቀጠ​ረ​በት፤ እነ​ር​ሱም ተከ​ት​ለ​ውት ሄዱ።


በሰ​ቂ​ማም ግንብ ውስጥ የነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ በዓል ቤት ወደ ምሽጉ ውስጥ ገቡ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos