ተመልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአማሌቅን አለቆች ሁሉና በአሳሶን ታማር የሚኖሩ አሞራውያንንም ገደሉአቸው።
ዘኍል 20:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፤ ተቀበረችም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ወደ ጺን ምድረ በዳ መጥተው በቃዴስ ተቀመጡ፤ እዚያ ማርያም ሞተች፤ ተቀበረችም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፥ በዚያም ተቀበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጥተው በቃዴስ ሰፈሩ፤ ማርያምም ስለሞተች በዚያው ተቀበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፥ በዚያም ተቀበረች። |
ተመልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአማሌቅን አለቆች ሁሉና በአሳሶን ታማር የሚኖሩ አሞራውያንንም ገደሉአቸው።
የዚያም ሕፃን እኅት ለፈርዖን ልጅ፥ “ሕፃኑን ታጠባልሽ ዘንድ ሄጄ የምታጠባ ሴት ከዕብራውያን ሴቶች ልጥራልሽን?” አለቻት።
የደቡቡም ድንበር ከታማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብፅ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ይሆናል። የደቡቡም ድንበር ይህ ነው።
ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፤ እንደ በረዶም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፤ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።
ገሥግሠውም በቃዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።
ወደ እግዚአብሔርም ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፤ መልአክንም ልኮ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።
ሙሴም የአሮንን ልብስ አወጣ፤ ልጁንም አልዓዛርን አለበሰው፤ አሮንም በዚያ በተራራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ራስ ላይ ወረዱ።
የቆሬ ወገን፥ የቀዓት ወገን። ቀዓትም እንበረምን ወለደ። በግብፅ ሀገር እነዚህን ሌዋውያንን የወለደቻቸው የሌዊ ልጅ የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።
እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አላከበራችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የክርክር ውኃ ነው።”
ከጋስዮንጋቤርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከጺን ምድረ በዳም ተጕዘው በፋራን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ይህችም ቃዴስ ናት።
የዛሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለባቸው ተዋጊዎች የሆኑ የዚያች ትውልድ ሰዎች ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።
በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በክርክር ውኃ ለቃሌ አልታዘዛችሁምና፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል አልቀደሳችሁኝምና፥