Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለቤቱ መመ​ረቅ ምስ​ጋና የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 አቤቱ፥ ተቀ​ብ​ለ​ኸ​ኛ​ልና፥ የጠ​ላ​ቶቼ መዘ​ባ​በቻ አላ​ደ​ረ​ግ​ኸ​ኝ​ምና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

2 አቤቱ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ይቅ​ርም አል​ኸኝ።

3 አቤቱ፥ ነፍ​ሴን ከሲ​ኦል አወ​ጣ​ሃት፥ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ለይ​ተህ አዳ​ን​ኸኝ።

4 ጻድ​ቃን ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፥ ለቅ​ድ​ስ​ና​ውም መታ​ሰ​ቢያ አመ​ስ​ግኑ።

5 መቅ​ሠ​ፍቱ ከቍ​ጣው ነውና፥ መዳ​ንም ከፈ​ቃዱ ነውና፤ ማታ ልቅሶ ይሰ​ማል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆ​ናል።

6 እኔም በደ​ስ​ታዬ፥ “ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ታ​ወ​ክም” አልሁ።

7 አቤቱ፥ በፈ​ቃ​ድህ ለሕ​ይ​ወቴ ኀይ​ልን ስጣት፤ ፊት​ህን መለ​ስህ፥ እኔም ደነ​ገ​ጥሁ።

8 አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ወደ አም​ላ​ኬም ለመ​ንሁ።

9 ወደ ጥፋት ብወ​ርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ? አፈር ያመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ልን? ጽድ​ቅ​ህ​ንም ይና​ገ​ራ​ልን?

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ፥ ይቅ​ርም አለኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ሆነኝ።

11 ልቅ​ሶ​ዬን መል​ሰህ ደስ አሰ​ኘ​ኸኝ። ማቄን ቀድ​ደህ ደስ​ታን አስ​ታ​ጠ​ቅ​ኸኝ።

12 ክብሬ እን​ዲ​ዘ​ም​ር​ልህ እን​ዳ​ል​ደ​ነ​ግ​ጥም፥ አቤቱ፥ አም​ላኬ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos