Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘዳግም 2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


እስ​ራ​ኤል በበ​ረሃ የዞ​ሩ​ባ​ቸው ዓመ​ታት

1 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ለኝ ተመ​ል​ሰን በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴ​ይ​ር​ንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦

3 ‘ይህን ተራራ መዞር ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ተመ​ል​ሳ​ችሁ ወደ መስዕ ሂዱ።’

4 ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ በሴ​ይር ላይ በተ​ቀ​መ​ጡት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በዔ​ሳው ልጆች ሀገር ታል​ፋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ርሱ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ እን​ግ​ዲህ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።

5 የሴ​ይ​ርን ተራራ ለዔ​ሳው ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከም​ድ​ራ​ቸው የጫማ መር​ገጫ ታህል እን​ኳን አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና አት​ጣ​ሉ​አ​ቸው።

6 ከእ​ነ​ርሱ በገ​ን​ዘብ ምግብ ገዝ​ታ​ችሁ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገ​ን​ዘብ በመ​ለ​ኪያ ገዝ​ታ​ችሁ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።

7 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ጅ​ህን ሥራ ሁሉ ባር​ኮ​ል​ሃ​ልና፤ ይህን ታላ​ቅና የሚ​ያ​ስ​ፈራ ምድረ በዳ እን​ዴት እንደ ዞር​ኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነበረ፤ ከተ​ና​ገ​ር​ኸው ሁሉ አን​ዳ​ችም አላ​ሳ​ጣ​ህም።

8 በሴ​ይ​ርም ከተ​ቀ​መ​ጡት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከዔ​ሳው ልጆች በዓ​ረባ መን​ገድ ከኤ​ሎ​ንና ከጋ​ስ​ዮን-ጋብር አለ​ፍን። ተመ​ል​ሰ​ንም በሞ​ዓብ ምድረ በዳ መን​ገድ አለ​ፍን።

9 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ እኔ አሮ​ኤ​ርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከም​ድሩ ርስት አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን አት​ጣላ፤ በሰ​ል​ፍም አት​ው​ጋ​ቸው።

10 እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ ሕዝብ ኀያ​ላ​ንም የሆኑ ኦሚ​ና​ው​ያን አስ​ቀ​ድሞ በዚያ ይቀ​መጡ ነበር።

11 እነ​ር​ሱም ደግሞ እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ራፋ​ይም ተብ​ለው ይታ​ወቁ ነበር፤ ሞዓ​ባ​ው​ያን ግን “ኦሚን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸው ነበር።

12 ሖራ​ው​ያ​ንም ደግሞ አስ​ቀ​ድሞ በሴ​ይር ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ የዔ​ሳው ልጆች ግን መቱ​አ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠው በር​ስቱ ምድር እስ​ራ​ኤል እን​ዳ​ደ​ረገ፥ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።

13 አሁ​ንም ‘ተነ​ሡና ተጓዙ፤ የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ ተሻ​ገሩ፤’ የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ ተሻ​ገ​ርን።

14 የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ እስከ ተሻ​ገ​ር​ን​በት ድረስ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማለ​ባ​ቸው ተዋ​ጊ​ዎች የሆኑ የዚ​ያች ትው​ልድ ሰዎች ከሰ​ፈሩ መካ​ከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃ​ዴስ በርኔ የተ​ጓ​ዝ​ን​በት ዘመን ሠላሳ ስም​ንት ዓመት ሆነ።

15 ከሰ​ፈ​ርም መካ​ከል ተለ​ይ​ተው እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላ​ያ​ቸው ነበረ።

16 “እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ተዋ​ጊ​ዎቹ ከጠፉ፥ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ከሞቱ በኋላ፥

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦

18 ‘አንተ ዛሬ የሞ​ዓ​ብን ዳርቻ አሮ​ኤ​ርን ታል​ፋ​ለህ፤

19 ለሎ​ጥም ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከአ​ሞን ልጆች ምድር ርስት አል​ሰ​ጥ​ህ​ምና በአ​ሞን ልጆች አቅ​ራ​ቢያ ስት​ደ​ርስ አት​ጣ​ላ​ቸው፤ አት​ው​ጋ​ቸ​ውም።’

20 ያም ደግሞ የራ​ፋ​ይም ምድር ተብሎ ተቈ​ጠረ፤ ራፋ​ይ​ምም አስ​ቀ​ድሞ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበረ፤ አሞ​ና​ው​ያን ግን “ዘም​ዞ​ማ​ው​ያን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።

21 እነ​ር​ሱም እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ፥ ጽኑ​ዓ​ንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም አሳ​ድ​ደው በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።

22 ሖራ​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ቸው አጥ​ፍቶ በሴ​ይር ለተ​ቀ​መ​ጡት ለዔ​ሳው ልጆች እን​ዳ​ደ​ረገ እነ​ርሱ ወረ​ሱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​መጡ።

23 እስከ ጋዛም ድረስ በአ​ሴ​ሮት ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩ​ትን ኤዋ​ው​ያ​ን​ንና ከቀ​ጰ​ዶ​ቅያ የወጡ ቀጰ​ዶ​ቃ​ው​ያ​ንን አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ ተቀ​መጡ።

24 ደግ​ሞም አለ፦ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ የአ​ር​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ተሻ​ገሩ፤ እነሆ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ግዛት፤ ውረ​ሳት፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ተዋጋ።

25 ከሰ​ማይ በታች ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ማስ​ደ​ን​ገ​ጥ​ህ​ንና ማስ​ፈ​ራ​ት​ህን እሰ​ድድ ዘንድ ዛሬ እጀ​ም​ራ​ለሁ፤ ስም​ህን በሰሙ ጊዜ በፊ​ትህ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ድን​ጋ​ጤም ይይ​ዛ​ቸ​ዋል።


እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሴዎ​ንን ድል እንደ አደ​ረጉ (ዘኍ​. 21፥ 21-30)

26 “ከቄ​ድ​ሞ​ትም ምድረ በዳ የሰ​ላ​ምን ቃል ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ወደ ሐሴ​ቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እን​ዲህ ብዬ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክሁ፦

27 ‘በሀ​ገ​ርህ ላይ ልለፍ፤ በአ​ውራ ጎዳና እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አል​ተ​ላ​ለ​ፍም።

28 የም​በ​ላ​ውን ምግብ በገ​ን​ዘብ ሽጥ​ልኝ፤ የም​ጠ​ጣ​ው​ንም ውኃ በገ​ን​ዘብ ስጠኝ፤ በእ​ግሬ ብቻ ልለፍ፤

29 በሴ​ይር የተ​ቀ​መጡ የዔ​ሳው ልጆች፥ በአ​ሮ​ዔ​ርም የተ​ቀ​መጡ ሞዓ​ባ​ው​ያን እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ልኝ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጠን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን እስ​ክ​ሻ​ገር ድረስ በእ​ግሬ ልለፍ።

30 የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳ​ል​ፈን ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን አደ​ን​ድ​ኖ​ታ​ልና፥ ልቡ​ንም አጽ​ን​ቶ​ታ​ልና።

31 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ አሞ​ራ​ዊ​ውን ሴዎ​ን​ንና ምድ​ሩን በፊ​ትህ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ መስ​ጠት እነሆ፥ ጀመ​ርሁ፤ ምድ​ሩን ትገዛ ዘንድ መው​ረስ ጀምር’ አለኝ።

32 ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡም ሁሉ ሊዋ​ጉን ወደ ኢያሳ ወጡ።

33 አም​ላ​ካ​ች​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን፤ እር​ሱ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ መታን።

34 በዚ​ያን ጊዜም ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ወሰ​ድን፤ ከተ​ማ​ው​ንም ሁሉ፥ ሴቶ​ች​ንም፥ ሕፃ​ኖ​ች​ንም አጠ​ፋን፤ አን​ዳ​ችም የሸሸ በሕ​ይ​ወት አላ​ስ​ቀ​ረ​ንም፥

35 ለእኛ ከማ​ረ​ክ​ና​ቸው ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ከወ​ሰ​ድ​ነው ምርኮ በቀር።

36 በአ​ር​ኖን ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔ​ርና በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ካለ​ችው ከተማ ጀም​ረን እስከ ገለ​ዓድ ተራራ ድረስ ማን​ኛ​ዪ​ቱም ከተማ አላ​መ​ለ​ጠ​ች​ንም፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን።

37 ዳሩ ግን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያ​ቦ​ቅም ወንዝ አጠ​ገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር ወደ አሉ ከተ​ሞች አል​ደ​ረ​ስ​ንም።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos