ነህምያ 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካሪም ልጅ መልክያ፥ የፈሐት ሞዓብ ልጅም አሱብ ሌላውን ክፍልና የእቶኑን ግንብ ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካሪም ልጅ መልክያና የፈሐት ሞዓብ ልጅ አሱብ ሌላውን ክፍልና የእቶን ግንብ ተብሎ የሚጠራውን መልሰው ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐሪም ልጅ ማልኪያና የፓሐት ሞዓብ ልጅ ሐሹብ ሌላውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” አደሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሓሪም ልጅ ማልኪያና የፓሐትሞአብ ልጅ ሐሹብ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” ተብሎ የሚጠራውን ግንብ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካሪም ልጅ መልክያ፥ የፈሐት ሞዓብ ልጅም አሱብ ሌላውን ክፍልና የእቶኑን ግንብ አደሱ። |
ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ክፍል ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕዝቡም እኩሌታ በስተኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥