La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አስረውም ወሰዱት፤ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካሰሩትም በኋላ ወስደው ለገዢው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አስረውም ወሰዱት፤ ለገዢው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱና ለገዥው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 27:2
25 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​ውም ወደ​ዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዚያ መሠ​ዊ​ያ​ዉን ሠራ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ረበ​ረበ፤ ልጁን ይስ​ሐ​ቅ​ንም አስሮ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ በዕ​ን​ጨቱ ላይ በልቡ አስ​ተ​ኛው።


ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው።


ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለን፤ እናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን፤” አሉአቸው።


በዚያ ወራ​ትም ሰዎች ወደ እርሱ መጥ​ተው ጲላ​ጦስ ደማ​ቸ​ውን ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ጋር ስለ ቀላ​ቀ​ለው ስለ ገሊላ ሰዎች ነገ​ሩት።


ከእ​ነ​ር​ሱም ተለ​ይ​ተው ከሄዱ በኋላ፥ የሚ​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትን አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤ በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ያስ​ቱት ዘንድ ወደ መኳ​ን​ን​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት አሳ​ል​ፈው ሊሰ​ጡት ራሳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ጻ​ድቁ ሰላ​ዮ​ችን ወደ እርሱ ላኩ።


ሁሉም በሙሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጲላ​ጦስ ወሰ​ዱት።


በዚ​ያም ቀን ሄሮ​ድ​ስና ጲላ​ጦስ ተስ​ማሙ፤ ቀድሞ ጥል ነበ​ራ​ቸ​ውና።


ጢባ​ር​ዮስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አም​ስት ዓመት ጴን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ የይ​ሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮ​ድ​ስም በገ​ሊላ የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወን​ድሙ ፊል​ጶ​ስም የኢ​ጡ​ር​ያ​ስና የጥ​ራ​ኮ​ኒ​ዶስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳ​ን​ዮ​ስም የሳ​ብ​ላ​ኒስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥


ጭፍ​ሮ​ችና የሺ አለ​ቃው፥ የአ​ይ​ሁ​ድም ሎሌ​ዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዘው አሰ​ሩት።


ሐናም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ወደ ቀያፋ ላከው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ከቀ​ያፋ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ወሰ​ዱት፤ አይ​ሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሳይ​በሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ አል​ገ​ቡም።


ሄሮ​ድ​ስም ማለዳ ያቀ​ር​በው ዘንድ በወ​ደ​ደ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ጴጥ​ሮስ ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በሰ​ን​ሰ​ለት ታስሮ በሁ​ለት ወታ​ደ​ሮች መካ​ከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የወ​ኅኒ ቤቱን በር ይጠ​ብቁ ነበር።


የሻ​ለ​ቃ​ውም ቀረብ ብሎ ያዘው፤ በሁ​ለት ሰን​ሰ​ለ​ትም እን​ዲ​ታ​ሰር አዘዘ፤ “ምን​ድ​ነው? ምንስ አደ​ረገ?” ብሎም ጠየቀ።


ሊገ​ር​ፉ​ትም በአ​ጋ​ደ​ሙት ጊዜ ጳው​ሎስ በአ​ጠ​ገቡ የነ​በ​ረ​ውን የመቶ አለቃ፥ “የሮ​ማን ሰው ያለ ፍርድ ልት​ገ​ርፉ ይገ​ባ​ች​ኋ​ልን?” አለው።


ከዚ​ህም በኋላ ይመ​ረ​ም​ሩት ዘንድ የሚ​ሹት ተዉት፤ የሻ​ለ​ቃ​ውም ሮማዊ መሆ​ኑን በዐ​ወቀ ጊዜ“ ለምን አሰ​ር​ሁት?” ብሎ ፈራ።


ሁለት ዓመ​ትም ካለፈ በኋላ፥ ፊል​ክስ ተሻ​ረና ጶር​ቅ​ዮስ ፊስ​ጦስ የሚ​ባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእ​ርሱ ቦታ መጣ፤ ፊል​ክ​ስም በግ​ልጥ ለአ​ይ​ሁድ ሊያ​ዳላ ወደደ፤ ስለ​ዚ​ህም ጳው​ሎ​ስን እንደ ታሰረ ተወው።


ስለ​ዚ​ህም ላያ​ችሁ፥ ልነ​ግ​ራ​ች​ሁና ላስ​ረ​ዳ​ችሁ ወደ እኔ እን​ድ​ት​መጡ ማለ​ድ​ኋ​ችሁ፤ ስለ እስ​ራ​ኤል ተስፋ በዚህ ሰን​ሰ​ለት ታስ​ሬ​አ​ለ​ሁና።”


የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም አም​ላክ፥ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ የሰ​ጣ​ች​ሁ​ትን፥ እር​ሱም ሊተ​ወው ወዶ ሳለ በጲ​ላ​ጦስ ፊት የካ​ዳ​ች​ሁ​ትን ልጁን ኢየ​ሱ​ስን ገለ​ጠው።


በቀ​ባ​ኸው በቅ​ዱስ ልጅህ ላይ ሄሮ​ድ​ስና ጰን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ ከወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውና ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ጋር በእ​ው​ነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።


ምን​አ​ል​ባት በመ​ን​ገድ የሚ​ያ​ገ​ኘው ሰው ቢኖር ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እያ​ሰረ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ላሉት ምኵ​ራ​ቦች የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ ከሊቀ ካህ​ናቱ ለመነ።


ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤


ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።


ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ራ​ች​ኋ​ቸው እንደ ታሰ​ራ​ችሁ ሆና​ችሁ እስ​ረ​ኞ​ችን ዐስቡ፤ መከራ የጸ​ና​ባ​ቸ​ው​ንም በሥ​ጋ​ችሁ ከእ​ነሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ችሁ ሆና​ችሁ ዐስቡ።


እነ​ር​ሱም፥ “አስ​ረን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ል​ፈን ልን​ሰ​ጥህ መጥ​ተ​ናል” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “እና​ንተ እን​ዳ​ት​ገ​ድ​ሉኝ ማሉ​ልኝ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አሳ​ል​ፋ​ችሁ ስጡኝ፤ እና​ንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላ​ቸው።