Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 24:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ሁለት ዓመ​ትም ካለፈ በኋላ፥ ፊል​ክስ ተሻ​ረና ጶር​ቅ​ዮስ ፊስ​ጦስ የሚ​ባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእ​ርሱ ቦታ መጣ፤ ፊል​ክ​ስም በግ​ልጥ ለአ​ይ​ሁድ ሊያ​ዳላ ወደደ፤ ስለ​ዚ​ህም ጳው​ሎ​ስን እንደ ታሰረ ተወው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላም፣ ፊልክስ በጶርቅዮስ ፊስጦስ ተተካ፤ ፊልክስም አይሁድን ለማስደሰት ሲል፣ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ሁለት ዓመትም ከሞላ በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደታሰረ ተወው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከሁለት ዓመት በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ቦታ ተተካ፤ ፊልክስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ፈልጎ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ሁለት ዓመትም ከሞላ በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 24:27
15 Referencias Cruzadas  

ፊስ​ጦስ ግን አይ​ሁድ እን​ዲ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ወዶ ጳው​ሎ​ስን፥ “ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተህ ስለ​ዚህ ነገር በዚያ ከእኔ ዘንድ ልት​ከ​ራ​ከር ትሻ​ለ​ህን?” አለው።


በእ​ርሱ ዘንድ ብዙ ቀን ከቈዩ በኋላ ፊስ​ጦስ የጳ​ው​ሎ​ስን ነገር ለን​ጉሡ ነገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ፊል​ክስ በእ​ስር ቤት ትቶት የሄደ አንድ እስ​ረኛ ሰው በእ​ዚህ አለ።


አይ​ሁ​ድ​ንም ደስ እን​ዳ​ላ​ቸው አይቶ ጴጥ​ሮ​ስን ደግሞ ያዘው፤ ያን​ጊ​ዜም የፋ​ሲካ በዓል ነበር።


ፊስ​ጦ​ስም ወደ ቂሣ​ርያ ደርሶ ሦስት ቀን ሰነ​በተ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።


ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ።


አሁ​ንስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለሰው ብዬ አስ​ተ​ም​ራ​ለ​ሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰ​ኛ​ለ​ሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወ​ድስ የክ​ር​ስ​ቶስ ባሪያ አይ​ደ​ለ​ሁም።


አግ​ሪ​ጳም ፊስ​ጦ​ስን፥ “ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ባይል ኖሮ ይህ ሰው ይፈታ ዘንድ በተ​ገባ ነበር” አለው።


ጳው​ሎ​ስም በገ​ን​ዘቡ በተ​ከ​ራ​የው ቤት ሁለት ዓመት ተቀ​መጠ፤ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​በል ነበር።


ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን በቂ​ሣ​ርያ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ እር​ሱም ራሱ ወደ​ዚ​ያው በቶሎ እን​ደ​ሚ​ሄድ መለ​ሰ​ላ​ቸው።


“እን​ኪ​ያስ ከሳ​ሾ​ችህ ሲመጡ እን​ሰ​ማ​ሃ​ለን” አለው፤ በሄ​ሮ​ድ​ስም ግቢ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቁት አዘዘ።


ለዐ​መፅ ከብዙ ሰው ጋር አንድ አት​ሁን፤ ፍር​ድ​ንም ለማ​ጣ​መም ከብዙ ሰው ጋር አት​ጨ​መር።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መዱ ጐተ​ቱት፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም አወ​ጡት፤ ኤር​ም​ያ​ስም በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios