Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 22:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሊገ​ር​ፉ​ትም በአ​ጋ​ደ​ሙት ጊዜ ጳው​ሎስ በአ​ጠ​ገቡ የነ​በ​ረ​ውን የመቶ አለቃ፥ “የሮ​ማን ሰው ያለ ፍርድ ልት​ገ​ርፉ ይገ​ባ​ች​ኋ​ልን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ጳውሎስም በጠፍር ወጥረው ሊገርፉት ሲሉ፣ አጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ፣ “አንድን የሮም ዜጋ ያለ ፍርድ ለመግረፍ ሕግ ይፈቅድላችኋልን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በጠፈርም በገተሩት ጊዜ ጳውሎስ በአጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ “የሮሜን ሰው ያለ ፍርድ ትገርፉ ዘንድ ተፈቅዶላችኋልን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ነገር ግን በጠፍር ወጥረው ሊገርፉት ሲዘጋጁ ጳውሎስ አጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ “የሮም ዜግነት ያለውን ሰው ያለ ፍርድ ልትገርፉት ተፈቅዶላችኋልን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በጠፈርም በገተሩት ጊዜ ጳውሎስ በአጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ፦ የሮሜን ሰው ያለ ፍርድ ትገርፉ ዘንድ ተፈቅዶላችኋልን? አለው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 22:25
13 Referencias Cruzadas  

ጳው​ሎስ ግን፥ “እኛ የሮም ሰዎች ስን​ሆን፥ ያለ ፍርድ በአ​ደ​ባ​ባይ ገረ​ፉን፤ አሰ​ሩ​ንም፤ አሁ​ንም በስ​ውር ሊያ​ወ​ጡን ይሻሉ፤ አይ​ሆ​ንም፥ ራሳ​ቸው መጥ​ተው ያው​ጡን” አላ​ቸው።


እኔም፦ ተከ​ሳሹ በከ​ሳ​ሾቹ ፊት ሳይ​ቆም፥ ለተ​ከ​ሰ​ሰ​በ​ትም ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ፋንታ ሳያ​ገኝ ማንም ቢሆን አሳ​ልፎ መስ​ጠት የሮ​ማ​ው​ያን ሕግ አይ​ደ​ለም ብየ መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።


የመቶ አለ​ቃው ግን ጳው​ሎ​ስን ሊያ​ድ​ነው ወድ​ዶ​አ​ልና ምክ​ራ​ቸ​ውን እንቢ አለ፤ ዋና የሚ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም ዋኝ​ተው ወደ ምድር እን​ዲ​ወጡ አዘ​ዛ​ቸው።


ጳው​ሎ​ስም ከመቶ አለ​ቆች አን​ዱን ጠርቶ፥ “የሚ​ነ​ግ​ረው ነገር አለና ይህን ልጅ ወደ የሻ​ለ​ቃው አድ​ር​ስ​ልኝ” አለው።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሲዶና ደረ​ስን፤ ዩል​ዮ​ስም ለጳ​ው​ሎስ አዘ​ነ​ለት፤ ወደ ወዳ​ጆቹ እን​ዲ​ሄ​ድና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ር​ፍም ፈቀ​ደ​ለት።


ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣ​ልያ በመ​ር​ከብ እን​ሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳው​ሎስ ከሌ​ሎች እስ​ረ​ኞች ጋር አብሮ የአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ጭፍራ ለነ​በረ ዩል​ዮስ ለሚ​ባል የመቶ አለቃ ተሰጠ።


በቂ​ሳ​ር​ያም ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ ኢጣ​ሊቄ ለሚ​ሉት ጭፍ​ራም የመቶ አለቃ ነበር።


የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።


የመቶ አለቃውም መልሶ “ጌታ ሆይ! በቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፤ ብላቴናዬም ይፈወሳል።


ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤


የመቶ አለ​ቃ​ውም ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ሻለ​ቃው ሄደና፥ “ይህ ሰው ሮማዊ ነው፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ዕወቅ” ብሎ ነገ​ረው።


ይህን ሰው አይ​ሁድ ያዙት፤ ሊገ​ድ​ሉ​ትም ፈለጉ፤ ከወ​ታ​ደ​ሮ​ችም ጋር ተከ​ላ​ከ​ል​ሁ​ለት፥ የሮም ሰው መሆ​ኑ​ንም ዐውቄ አዳ​ን​ሁት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios