ዘሌዋውያን 11:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በድን የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእነዚህንም በድን የሚያነሣ ሰው ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ ሆኖም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድናቸውንም የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም በድን የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም በድን የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው። |
ሰኰናም ያለው፥ ነገር ግን ሰኰናው ያልተሰነጠቀ፥ የማያመሰኳም እንስሳ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ እርሱን የሚነካ ሁሉ ርኩስ ነው።
ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ በድኑንም የሚያነሣ፤ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።
ደግሞ በሰባተኛው ቀን ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ያች ደዌ ብትከስም፥ በቆዳውም ላይ ባትሰፋ፥ ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለዋል፤ ምልክት ነውና፥ ልብሱንም አጥቦ ንጹሕ ይሆናል።
የነጻውም ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ጠጕሩንም ሁሉ ይላጫል፤ በውኃም ይታጠባል፤ ንጹሕም ይሆናል። ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።
“ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው ከፈሳሹ ነገር ሲነጻ ስለ መንጻቱ ሰባት ቀን ይቈጥራል፤ ልብሶቹንም ያጥባል፤ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠባል፤ ንጹሕም ይሆናል።
ካህኑም አንዲቱን ለኀጢአት መሥዋዕት፥ አንዲቱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስተሰርይለታል።
ለመለቀቅ የሚሆነውን ፍየል የወሰደ ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል።
የሞተውን ወይም አውሬ የሰበረውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የሀገር ልጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፤ በውኃም ይታጠባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
የጊደሪቱንም አመድ ያከማቸው ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ገላውንም ይታጠባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ይህም ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸውም ለሚኖር መጻተኛ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
ንጹሑም በሦስተኛው ቀንና በሰባተኛው ቀን በርኩሱ ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ይነጻል፤ እርሱም ልብሱን ያጥባል፤ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።
ካህኑም ልብሱን ያጥባል፤ ገላውንም በውሃ ይታጠባል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል፤ ካህኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆናል።
ጴጥሮስም፥ “መቼም ቢሆን አንተ እግሬን አታጥበኝም” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ እኔ እግርህን ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል ፋንታ የለህም” ብሎ መለሰለት።
እንግዲህ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ።
እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥምቀትም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዐቶች ብቻ ናቸው።
ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፤ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።