Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 14:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 በተ​ዘ​ጋ​በ​ትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚ​ገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 “ቤቱ ተዘግቶ ሳለ ማንኛውም ሰው ቢገባበት፣ ያ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 በተዘጋበትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ከተዘጋ በኋላ ወደዚያ ቤት የገባ ሰው ሁሉ እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሆናል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 በተዘጋበትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 14:46
14 Referencias Cruzadas  

በአ​ራት እግ​ሮቹ ከሚ​ሄድ እን​ስሳ ሁሉ በመ​ዳ​ፎቹ ላይ የሚ​ሄድ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው፤ የእ​ር​ሱን በድን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


በድ​ና​ቸ​ው​ንም የሚ​ያ​ነሣ ልብ​ሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው። እነ​ር​ሱም በእ​ና​ንተ ዘንድ ርኩ​ሳን ናቸው።


ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱት ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ርኩ​ሳን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸ​ውን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸው በም​ንም ላይ ቢወ​ድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የዕ​ን​ጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቍር​በት ወይም ከረ​ጢት ቢሆን የሚ​ሠ​ራ​በት ዕቃ ሁሉ እር​ሱን በውኃ ውስጥ ይን​ከ​ሩት፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።


“ለመ​ብል ከሚ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ እን​ስ​ሳት የሞተ ቢኖር፥ በድ​ኑን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከበ​ድ​ኑም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ በድ​ኑ​ንም የሚ​ያ​ነሣ፤ ልብ​ሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


በቤ​ቱም የሚ​ተኛ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ በቤ​ቱም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


ከበ​ታ​ቹም ያለ​ውን ነገር የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ነገ​ሮች የሚ​ያ​ነሣ ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


የሞ​ተ​ውን ወይም አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን የሚ​በላ ሰው ሁሉ፥ የሀ​ገር ልጅ ወይም እን​ግዳ ቢሆን፥ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።


እነ​ዚ​ህን ሁሉ የሚ​ነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ገላ​ውን በውኃ ካል​ታ​ጠበ ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos