Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘኍል 31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


በም​ድ​ያ​ማ​ው​ያን ላይ የተ​ደ​ረገ ጦር​ነት
( ዘዳ. 3፥12-22 )

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

2 “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቀል ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን ተበ​ቀል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ወገ​ኖ​ችህ ትጨ​መ​ራ​ለህ።”

3 ሙሴም ለሕ​ዝቡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ሰዎ​ችን አስ​ታ​ጥቁ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምድ​ያ​ምን ይበ​ቀሉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከም​ድ​ያም ጋር ይሰ​ለፉ።

4 ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ሁሉ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦር​ነት ስደዱ፤”

5 ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አእ​ላ​ፋት፥ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሺህ ቈጠሩ፤ ለጦ​ር​ነት የተ​ሰ​ለ​ፉ​ትም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሆኑ።

6 ሙሴም ከየ​ነ​ገዱ አንድ ሺህ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸ​ውና ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ከፊ​ን​ሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋ​ያተ ቅድ​ሳ​ቱና ምል​ክት መስጫ መለ​ከ​ቶ​ችም በእ​ጆ​ቻ​ቸው ነበሩ።

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ከም​ድ​ያም ጋር ተዋጉ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሁሉ ገደሉ።

8 የም​ድ​ያ​ም​ንም ነገ​ሥ​ታት በዚ​ያው ጦር​ነት በአ​ን​ድ​ነት ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ አም​ስ​ቱም የም​ድ​ያም ነገ​ሥ​ታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሮባቅ ነበሩ፤ የቢ​ዖ​ር​ንም ልጅ በለ​ዓ​ምን ደግሞ በዚ​ያው ጦር​ነት በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።

9 የም​ድ​ያ​ም​ንም ሴቶ​ችና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ማረኩ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዕቃ​ቸ​ውን፥ ንብ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና ኀይ​ላ​ቸ​ውን በዘ​በዙ።

10 የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ውን ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ሰፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።

11 ከሰው እስከ እን​ስሳ ምር​ኮ​አ​ቸ​ው​ንና ብዝ​በ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ ወሰዱ።

12 የማ​ረ​ኩ​ትን ምር​ኮ​ው​ንና የዘ​ረ​ፉ​ትን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ወዳ​ለው ሰፈር አመጡ።


የሠ​ራ​ዊቱ ከጦ​ር​ነት መመ​ለስ

13 ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም፥ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ሊገ​ና​ኙ​አ​ቸው ወጡ።

14 ሙሴም ከዘ​መቻ በተ​መ​ለ​ሱት በጭ​ፍራ አለ​ቆች፥ በሻ​ለ​ቆ​ችና በመቶ አለ​ቆች ላይ ተቈጣ።

15 ሙሴም አላ​ቸው፥ “ሴቶ​ችን ሁሉ ለምን አዳ​ና​ች​ኋ​ቸው?

16 እነ​ርሱ በበ​ለ​ዓም ምክር በፌ​ጎር ምክ​ን​ያት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የሚ​ያ​ስቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል እን​ዲ​ስቱ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ዕን​ቅ​ፋ​ቶች ናቸ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ላይ መቅ​ሠ​ፍት ሆኖ​አል፤

17 አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ወን​ዱን ሁሉ በአ​ለ​በት ግደሉ፥ ወን​ድ​ንም የም​ታ​ው​ቀ​ውን ሴት ሁሉ ግደሉ።

18 ወን​ድን የማ​ያ​ው​ቁ​ትን ሴቶች ልጆ​ችን ሁሉ ግን አድ​ኑ​አ​ቸው።

19 እና​ን​ተም ከሰ​ፈሩ ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ሰውን የገ​ደለ ሁሉ፥ የተ​ገ​ደ​ለ​ው​ንም የዳ​ሰሰ ሁሉ፥ እና​ን​ተና የማ​ረ​ካ​ች​ኋ​ቸ​ውም በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ንጹሕ አድ​ርጉ።

20 ልብ​ስ​ንም፥ ከቁ​ር​በ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ውን ሁሉ፥ ከፍ​የ​ልም ጠጕር፥ ከዕ​ን​ጨ​ትም የተ​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ንጹሕ አድ​ርጉ።”

21 ካህ​ኑም አል​ዓ​ዛር ከሰ​ልፍ የመ​ጡ​ትን ሰዎች አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ያዘ​ዘው የሕጉ ሥር​ዐት ይህ ነው፤

22 ወር​ቁና ብሩ፥ ናሱም፥ ብረ​ቱም፥ ቆር​ቆ​ሮ​ውም፥ እር​ሳ​ሱም፥

23 በእ​ሳት ለማ​ለፍ የሚ​ች​ለው ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ ይሆ​ናል፤ ነገር ግን በማ​ን​ጻት ውኃ ደግሞ ይጠ​ራል። በእ​ሳ​ትም ለማ​ለፍ የማ​ይ​ች​ለ​ውን በውኃ ታሳ​ል​ፉ​ታ​ላ​ችሁ።

24 በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ልብ​ሳ​ች​ሁን እጠቡ፤ ንጹ​ሓ​ንም ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።”


ምርኮ እንደ ተካ​ፈሉ

25 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

26 “አን​ተና ካህኑ አል​ዓ​ዛር፥ የማ​ኅ​በ​ሩም አባ​ቶች አለ​ቆች የተ​ማ​ረ​ኩ​ትን ሰውና እን​ስሳ ቍጠሩ።

27 ምር​ኮ​ው​ንም በተ​ዋ​ጉ​ትና ወደ ሰልፍ በወ​ጡት፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ መካ​ከል ትከ​ፍ​ላ​ላ​ችሁ።

28 ከእ​ነ​ዚ​ያም ከተ​ዋ​ጉት፥ ወደ ሰል​ፍም ከወ​ጡት ሰል​ፈ​ኞች ዘንድ ከሰ​ዎ​ችም፥ ከበ​ሬ​ዎ​ችም፥ ከበ​ጎ​ችም፥ ከአ​ህ​ዮ​ችም፥ ከአ​ም​ስት መቶ አንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግብር ታወ​ጣ​ላ​ችሁ።

29 ከድ​ር​ሻ​ቸው እኩ​ሌታ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።

30 ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ድርሻ እኩ​ሌታ፥ ከሰ​ዎ​ችም፥ ከበ​ሬ​ዎ​ችም፥ ከበ​ጎ​ችም፥ ከአ​ህ​ዮ​ችም፥ ከእ​ን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ ከአ​ምሳ አንድ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ለሌ​ዋ​ው​ያን ትሰ​ጣ​ለህ።”

31 ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።

32 ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎ​ችም ከወ​ሰ​ዱት ብዝ​በዛ የቀ​ረው ምርኮ እን​ዲህ ሆነ፤ ስድ​ስት መቶ ሰባ አም​ስት ሺህ በጎች፤

33 ሰባ ሁለት ሺህ በሬ​ዎች፥

34 ስድሳ አንድ ሺህ አህ​ዮች፥

35 ወንድ ከማ​ያ​ውቁ ሴቶ​ችም ሠላሳ ሁለት ሺህ ነፍስ።

36 በዘ​መ​ቻም ለነ​በሩ ሰዎች ድርሻ የሆነ እኩ​ሌታ ከበግ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ በጎች ነበሩ፤

37 ከበ​ጎ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግብር ስድ​ስት መቶ ሰባ አም​ስት ነበረ።

38 በሬ​ዎ​ችም ሠላሳ ስድ​ስት ሺህ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብር ሰባ ሁለት ነበረ።

39 አህ​ዮ​ቹም ሠላሳ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብር ስድሳ አንድ ነበረ።

40 ሰዎ​ቹም ዐሥራ ስድ​ስት ሺህ ነበሩ ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብር ሠላሳ ሁለት ነበረ።

41 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለ​ዩ​ትን ግብር ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ሰጠው።

42 ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እኩ​ሌ​ታም፥ ወደ ሰልፍ ከወ​ጡት ወን​ዶች ላይ ሙሴ የለ​የው፥

43 የማ​ኅ​በሩ ድርሻ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ በጎች፥

44 ሠላሳ ስድ​ስት ሺህ በሬ​ዎች፤

45 ሠላሳ ሺህ አም​ስት መቶ አህ​ዮች፥

46 ዐሥራ ስድ​ስት ሺህ ሰዎች ነበሩ።

47 ሙሴ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ድርሻ ከሰ​ውና ከእ​ን​ስሳ ከሃ​ምሳ አንድ ወሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ሌዋ​ው​ያን ሰጠ።

48 በሠ​ራ​ዊት አእ​ላ​ፋት ላይ የተ​ሾ​ሙት አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች ወደ ሙሴ ቀረቡ፤ ሙሴ​ንም እን​ዲህ አሉት፦

49 “ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ወደ ሰልፍ የወ​ጡ​ትን ከእ​ጃ​ችን በታች ያሉ​ትን ቈጠሩ፤ ከእ​ኛም አንድ አል​ጐ​ደ​ለም።

50 ሰውም ሁሉ ከአ​ገ​ኘው ከወ​ርቅ ዕቃ፥ ከእ​ግር አል​ቦም፥ ከአ​ም​ባ​ርም፥ ከቀ​ለ​በ​ትም ከጕ​ት​ቻም፥ ከድ​ሪ​ውም ስለ እኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታስ​ተ​ሰ​ር​ዩ​ልን ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አም​ጥ​ተ​ናል” አሉት።

51 ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም ወር​ቁ​ንና በልዩ ልዩ የተ​ሠ​ራ​ውን ዕቃ ሁሉ ከእ​ጃ​ቸው ተቀ​በሉ።

52 ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለ​ዩ​ትና ያቀ​ረ​ቡት ወርቅ ሁሉ ዐሥራ ስድ​ስት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ሰቅል ነበረ።

53 ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ የማ​ረ​ኩ​ትን ለየ​ራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።

54 ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም ወር​ቁን ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች ወሰዱ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ቡት።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos