Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 15:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው ከፈ​ሳሹ ነገር ሲነጻ ስለ መን​ጻቱ ሰባት ቀን ይቈ​ጥ​ራል፤ ልብ​ሶ​ቹ​ንም ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በም​ንጭ ውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው ከፈሳሹ ሲነጻ፣ በሕጉ መሠረት ለመንጻቱ ሰባት ቀን ይቍጠር፤ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በምንጭ ውሃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው ከፈሳሹ ነገር ሲነጻ፥ ስለ መንጻቱ ሰባት ቀን ይቈጥራል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠባል፥ እርሱም ንጹሕ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ፈሳሽ ያለበት ሰው ከፈሳሽ በሽታው በዳነ ጊዜ የነጻ እንዲሆን እስከ ሰባት ቀን ድረስ ይቈይ፤ ከዚያም በኋላ ልብሱን ይጠብ፤ በንጹሕ የምንጭ ውሃም ገላውን ይታጠብ፤ የነጻም ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው ከፈሳሹ ነገር ሲነጻ ስለ መንጻቱ ሰባት ቀን ይቈጥራል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 15:13
16 Referencias Cruzadas  

የነ​ጻ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ጠጕ​ሩ​ንም ሁሉ ይላ​ጫል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል። ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀ​መ​ጣል።


ሰባት ቀን ይክ​ና​ች​ኋ​ልና የክ​ህ​ነ​ታ​ችሁ ቀን እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ሰባት ቀን ከማ​ኅ​በሩ ድን​ኳን ደጃፍ አት​ውጡ።


ከፈ​ሳ​ሽ​ዋም ብት​ነጻ ሰባት ቀን ትቈ​ጥ​ራ​ለች፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጽ​ሕት ትሆ​ና​ለች።


መኝ​ታ​ው​ንም የሚ​ነካ ሰው ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ሰው​ነ​ቱን ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ! ልባችሁን አጥሩ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለ​ሆን ራሳ​ች​ንን እና​ንጻ፤ ሥጋ​ች​ንን አና​ር​ክስ፤ ነፍ​ሳ​ች​ን​ንም አና​ሳ​ድፍ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት የም​ን​ቀ​ደ​ስ​በ​ትን እን​ሥራ።


እኔ​ንም ከበ​ደ​ሉ​በት ኀጢ​አት ሁሉ አነ​ጻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም የበ​ደ​ሉ​ኝ​ንና ያመ​ፁ​ብ​ኝን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይቅር እላ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራ​ቁን በፊቷ ቢተ​ፋ​ባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገ​ባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰ​ፈር ውጭ ተዘ​ግታ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመ​ለስ” አለው።


“በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ዓመት የሞ​ላ​ቸ​ውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ት​ንም አን​ዲት የዓ​መት እን​ስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህ​ልም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይ​ትም ይወ​ስ​ዳል።


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠራ።


ሰባት ቀን መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።


“እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ሁሉ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ እን​ዲህ አድ​ርግ፤ ሰባት ቀን እጆ​ቻ​ቸ​ውን ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios