ለአብራምም ስለ እርስዋ መልካም አደረጉለት፤ ለእርሱ በጎችም፥ በሬዎችም፥ አህዮችም፥ በቅሎዎችም፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም፥ ግመሎችም ነበሩት።
ኢዮብ 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብቶቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አምስት መቶም እንስት አህዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት፤ ሥራውም በምድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብቱም ሰባት ሺሕ በጎች፣ ሦስት ሺሕ ግመሎች፣ ዐምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና ዐምስት መቶ እንስት አህዮች ነበረ፤ እጅግ ብዙ ባሮችም ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ከሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ታላቅ ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሀብቱም ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህም ግመሎች፥ አምስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አምስት መቶም እንስት አህዮች ነበረ፥ እጅግ ብዙም ባሪያዎች ነበሩት፥ ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ። |
ለአብራምም ስለ እርስዋ መልካም አደረጉለት፤ ለእርሱ በጎችም፥ በሬዎችም፥ አህዮችም፥ በቅሎዎችም፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም፥ ግመሎችም ነበሩት።
አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።
በአንድነትም ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቸውም፤ ንብረታቸው ብዙ ነበርና፤ ስለዚህም ባንድነት ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቻቸውም።
እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፤ አገነነውም፤ ላሞችንና በጎችን፥ ወርቅንና ብርን፥ ወንዶች ባሪያዎችንና ሴቶች ባሪያዎችን፥ ግመሎችንና አህዮችንም ሰጠው።
አብርሃምም ለቁባቶቹ ልጆች ሀብትን ሰጣቸው፤ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ምሥራቅ ሀገር ሰደዳቸው።
ያዕቆብም በማለዳ ተነሥቶ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም የሶርያ ሰው የባቱኤል ልጅ ወደሚሆን ወደ ላባ ሄደ።
መንጋቸውም፥ የጋማ ከብቶቻቸውም፥ ገንዘባቸውም ሁሉ ለእኛ አይደሉምን? ነገር ግን በዚህ ብቻ ከመሰልናቸው ከእኛ ጋር ይቀመጣሉ።”
ምናሔምም ብሩን ለአሶር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእስራኤል ባለጠጎች ሁሉ ላይ በእያንዳንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስገብሮ አወጣ። የአሶርም ንጉሥ ተመለሰ፤ በሀገሪቱም አልተቀመጠም።
የሞዓብም ንጉሥ ሞሳ ባለ በጎች ነበር፤ ለእስራኤልም ንጉሥ መቶ ሺህ የጠጕር አውራ በጎችንና መቶ ሺህ ጠቦቶችን ይገብርለት ነበር።
በምድረ በዳውም ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጕድጓድም ማሰ፤ በቆላውና በደጋው ብዙ እንስሶች ነበሩትና፤ ደግሞም እርሻ ይወድድ ነበርና በተራራማውና በፍሬያማው ስፍራ አራሾችና የወይን አትክልተኞች ነበሩት።
አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
ወንዶች ልጆቹም ሄደው በየተራ በእያንዳንዳቸው ቤት ግብዣ ያደርጉ ነበር፤ ሦስቱ እኅቶቻቸውንም ከእነርሱ ጋር ይወስዱአቸው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር ይበሉና ይጠጡ ነበር።
መንገዳቸውን መረመርሁ፤ እንደ አለቃም ሆኜ ተቀመጥሁ፤ ንጉሥ በሠራዊቱ መካከል እንደሚኖር ኖርሁ፤ በሚያዝኑም ጊዜ በእኔ ይጽናኑ ነበር።
እግዚአብሔርም ኢዮብን አዳነው። ኢዮብም ስለ ወዳጆቹ ጸለየ፥ እግዚአብሔርም ኀጢአታቸውን ተወላቸው፤ እግዚአብሔርም ቀድሞ በነበረው ገንዘቡ ሁሉ ፋንታ ሁለት እጥፍ ከዚያም በላይ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው።
እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፤ መንጋዎቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፤ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።
በምሳሌም ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ከሜስጴጦምያ ጠርቶ አመጣኝ፤ ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ” ብሎ።
የእስራኤልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያንና አማሌቃውያን ይዘምቱባቸው ነበር፥ በምሥራቅም የሚኖሩ ልጆች አብረው ይዘምቱባቸው ነበር፤
እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው በብዛት እንደ አንበጣ ሆነው ይመጡባቸው ነበር፤ ለእነርሱና ለግመሎቻቸው ቍጥር አልነበራቸውም፤ ምድሪቱንም ያጠፏት ዘንድ ይመጡ ነበር።
ብዛታቸውም እንደ አንበጣ የሆነ ምድያማውያንና አማሌቃውያን የምሥራቅም ልጆች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት ቍጥር እንደሌለው በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበረ።
ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር በቀርቀር ነበሩ፤ ሰይፍ የሚመዝዙ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና ከምሥራቅ ሰዎች ሠራዊት ሁሉ የቀሩ ዐሥራ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ።
በማዖንም የተቀመጠ አንድ ሰው ነበረ፤ ከብቱም በቀርሜሎስ ነበረ፤ እጅግም ታላቅ ሰው ነበረ፤ ለእርሱም ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት፤ በቀርሜሎስም በጎቹን ሊሸልት ሄደ።
ዳዊትም ሀገሪቱን መታ፤ ወንድም ሆነ፥ ሴትም ሆነ፥ ማንንም በሕይወት አልተወም፤ በጎችንና ላሞችን፥ አህያዎችንና ግመሎችን፥ ልብስንም ማረከ፤ ተመልሶም ወደ አንኩስ መጣ።