Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ነገሥት 15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ሜ​ስ​ያስ ልጅ ዓዛ​ር​ያስ ነገሠ።

2 ዓዛ​ር​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ኮልያ የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች።

3 አባቱ አሜ​ስ​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ።

4 ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ በነ​በ​ሩት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንጉ​ሡን በደዌ ዳሰ​ሰው፤ እስ​ከ​ሚ​ሞ​ት​በ​ትም ቀን ለም​ጻም ሆነ፤ በተ​ለየ ቤትም ይቀ​መጥ ነበር፤ የን​ጉ​ሡም ልጅ ኢዮ​አ​ታም በን​ጉሡ ቤት ላይ ሠል​ጥኖ ለሀ​ገሩ ሕዝብ ይፈ​ርድ ነበር።

6 የቀ​ረ​ውም የዓ​ዛ​ር​ያስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

7 ዓዛ​ር​ያ​ስም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም ኢዮ​አ​ታም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

8 በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በሠ​ላሳ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ልጅ ዘካ​ር​ያስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ስድ​ስት ወር ነገሠ።

9 አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ታ​ቸው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም።

10 የኢ​ያ​ቢ​ስም ልጅ ሴሎም፤ ሌሎ​ችም ከዱት፤ በይ​ብ​ል​ዓም መት​ተው ገደ​ሉት፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ሴሎም ነገሠ።

11 የቀ​ረ​ውም የዘ​ካ​ር​ያስ ነገር፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

12 ለኢዩ፥ “ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” ተብሎ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነበረ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።

13 በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በሠ​ላሳ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት የኢ​ያ​ቢስ ልጅ ሴሎም ነገሠ፤ በሰ​ማ​ር​ያም አንድ ወር ነገሠ።

14 የጋ​ዲም ልጅ ምና​ሔም ከቴ​ር​ሳ​ላቅ ወጥቶ ወደ ሰማ​ርያ ሄደ፤ በሰ​ማ​ር​ያም የኢ​ያ​ቢ​ስን ልጅ ሴሎ​ምን መታ፤ ገደ​ለ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።

15 የቀ​ረ​ውም የሴ​ሎም ነገር፥ የተ​ማ​ማ​ለ​ውም ዐመፅ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሓፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

16 በዚያ ጊዜም ምና​ሔም ቴር​ሳን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ሁሉ፥ ዳር​ቻ​ዋ​ንም መታ፤ ይከ​ፍ​ቱ​ለ​ትም ዘንድ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና መታት፤ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን እር​ጉ​ዞች ሁሉ ሰነ​ጠ​ቃ​ቸው።

17 በይ​ሁዳ ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በሠ​ላሳ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት የጋዲ ልጅ ምና​ሔም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዐሥር ዓመት ነገሠ።

18 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አ​ትም አል​ራ​ቀም።

19 በዘ​መ​ኑም የአ​ሶር ንጉሥ ፎሐ በም​ድ​ሪቱ ላይ ወጣ፤ ምና​ሔ​ምም የፎሐ እጅ ከእ​ርሱ ጋር እን​ዲ​ሆን አንድ ሺህ መክ​ሊት ብር ሰጠው።

20 ምና​ሔ​ምም ብሩን ለአ​ሶር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእ​ስ​ራ​ኤል ባለ​ጠ​ጎች ሁሉ ላይ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስ​ገ​ብሮ አወጣ። የአ​ሶ​ርም ንጉሥ ተመ​ለሰ፤ በሀ​ገ​ሪ​ቱም አል​ተ​ቀ​መ​ጠም።

21 የቀ​ረ​ውም የም​ና​ሔም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

22 ምና​ሔ​ምም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፤ ልጁም ፋቂ​ስ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

23 በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በአ​ም​ሳ​ኛው ዓመት የም​ና​ሔም ልጅ ፋቂ​ስ​ያስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ሁለት ዓመ​ትም ነገሠ።

24 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አ​ትም አል​ራ​ቀም።

25 የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰ​ማ​ር​ያም በን​ጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአ​ር​ጎ​ብና ከአ​ርያ ጋር መታው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደ​ለ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።

26 የቀ​ረ​ውም የፋ​ቂ​ስ​ያስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

27 በይ​ሁዳ ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በአ​ምሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ሃያ ዓመ​ትም ነገሠ።

28 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አ​ትም አል​ራ​ቀም።

29 በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።

30 በዖ​ዝ​ያ​ንም ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም በሃ​ያ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮ​ሜ​ልዮ ልጅ በፋ​ቁሔ ላይ ዐመ​ፀ​በት፤ መት​ቶም ገደ​ለው፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።

31 የቀ​ረ​ውም የፋ​ቁሔ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

32 በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በሮ​ሜ​ልዩ ልጅ በፋ​ቁሔ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የይ​ሁዳ ንጉሥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ ኢዮ​አ​ታም ነገሠ።

33 መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ ሃያ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የሳ​ዶቅ ልጅ ኢየ​ሩሳ ነበ​ረች።

34 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ አባቱ ዓዛ​ር​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ።

35 ነገር ግን የጣ​ዖ​ታ​ቱን ቤት አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ ይሠ​ዉና ያጥኑ ነበር። እር​ሱም የላ​ይ​ኛ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በር ሠራ።

36 የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ታም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

37 በዚ​ያም ወራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሶ​ር​ያን ንጉሥ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ፋቁ​ሔን በይ​ሁዳ ላይ መላክ ጀመረ።

38 ኢዮ​አ​ታ​ምም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ ልጁም አካዝ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos