2 ነገሥት 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ምናሔምም ብሩን ለአሶር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእስራኤል ባለጠጎች ሁሉ ላይ በእያንዳንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስገብሮ አወጣ። የአሶርም ንጉሥ ተመለሰ፤ በሀገሪቱም አልተቀመጠም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ምናሔም ገንዘቡ እንዲዋጣ ያደረገው ከእስራኤል ሲሆን፣ ይህንም ያደረገው ለአሦር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ እያንዳንዱ ሀብታም ዐምሳ፣ ዐምሳ ሰቅል ብር እንዲያዋጣ በማስገደድ ነበር። ስለዚህ የአሦር ንጉሥ በዚያች አገር አልቈየም፤ ተመልሶ ሄደ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ምናሔም ገንዘቡን የሰበሰበው የእስራኤል ከበርቴዎች እያንዳንዳቸው ኀምሳ ጥሬ ብር አዋጥተው እንዲሰጡ በማስገደድ ነበር። በዚህም ዓይነት ቲግላት ፐሌሴር በሰላም ወደ አገሩ ተመልሶ ሄደ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ምናሔም ገንዘቡን የሰበሰበው የእስራኤል ከበርቴዎች እያንዳንዳቸው ኀምሳ ጥሬ ብር አዋጥተው እንዲሰጡ በማስገደድ ነበር። በዚህም ዐይነት ቲግላት ፐሌሴር በሰላም ወደ አገሩ ተመልሶ ሄደ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ምናሔምም ብሩን ለአሦር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ በእስራኤል ባለ ጠጎች ሁሉ ላይ በእያንዳንዱ ላይ አምሳ ሰቅል ብር አስገብሮ አወጣ። የአሦርም ንጉሥ ተመለሰ፤ በአገሪቱም አልተቀመጠም። Ver Capítulo |