Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 49:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ስለ መታ​ቸው ስለ ቄዳ​ርና ስለ አሦር መን​ግ​ሥ​ታት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተነሡ ወደ ቄዳ​ርም ውጡ፤ የም​ሥ​ራ​ቅ​ንም ልጆች አጥፉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ወጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት የተነገረ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተነሡ፣ ቄዳርን ውጉ፤ የምሥራቅንም ሕዝብ ደምስሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ድል ስላደረጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፥ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ድል ስላደረጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተነሡ፤ በቄዳር ሕዝብ ላይ ዝመቱ፤ የምሥራቅንም ሕዝብ አጥፉ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታ ስለ ቄዳርና ስለ አሶር መንግሥታት፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፥ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 49:28
20 Referencias Cruzadas  

በባ​ሕ​ርም በኩል በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መር​ከ​ቦች ላይ እየ​በ​ረሩ ይወ​ር​ዳሉ፤ የም​ሥ​ራቅ ሰዎ​ች​ንና ኤዶ​ም​ያ​ስን በአ​ን​ድ​ነት ይዘ​ር​ፋሉ፤ በሞ​ዓብ ላይ ቀድ​መው እጃ​ቸ​ውን ይዘ​ረ​ጋሉ፤ የአ​ሞ​ንም ልጆች ቀድ​መው ለእ​ነ​ርሱ ይታ​ዘ​ዛሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም የሚ​ኖሩ ልጆች አብ​ረው ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፤


የይ​ስ​ማ​ኤ​ልም የል​ጆቹ ስም በየ​ስ​ማ​ቸ​ውና በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እን​ዲህ ነው።


ዓረ​ብና የቄ​ዳር አለ​ቆች ሁሉ የእ​ጅሽ ነጋ​ዴ​ዎች ነበሩ፤ በግ​መ​ሎ​ችና በአ​ውራ በጎች፥ በፍ​የ​ሎ​ችም በእ​ነ​ዚህ ከአ​ንቺ ጋር ይነ​ግዱ ነበር።


“ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰም​ቻ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛብ ሀገ​ሮች ተሰ​ብ​ሰቡ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ኑ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ውጓት፥ የሚል መል​እ​ክ​ተኛ ተል​ኳል።


ወደ ኬቲም ደሴ​ቶች እለ​ፉና ተመ​ል​ከቱ፤ ወደ ቄዳ​ርም ላኩና እጅግ መር​ምሩ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ያለ ነገር ሆኖ እንደ ሆነ እዩ።


አሦ​ርም የወ​ፎች መኖ​ሪ​ያና የዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ በዚ​ያም ሰው አይ​ኖ​ርም፤ የሰው ልጅም አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም።


ምድረ በዳ​ውና ከተ​ሞ​ችዋ፥ የቄ​ዳ​ርም ነዋ​ሪ​ዎ​ችና መን​ደ​ሮች ድም​ፃ​ቸ​ውን ያንሡ፤ በዋ​ሻም የሚ​ኖሩ እልል ይበሉ፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።


ሌሊ​ትም በዲ​ዳ​ና​ው​ያን ጎዳና በዛ​ፎች ውስጥ ታድ​ራ​ለህ፤


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድን​ኳ​ኖች እንደ ሰሎ​ሞ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች።


ከብ​ቶ​ቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመ​ሎች፥ አም​ስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አም​ስት መቶም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት፤ ሥራ​ውም በም​ድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በም​ሥ​ራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።


ትው​ል​ዳ​ቸ​ውም እን​ደ​ዚህ ነው። የይ​ስ​ማ​ኤል በኵር ልጅ ናቢ​ዎት፤ ቄዳር፥ ቢዲ​ሄል፥ ሙባ​ሳን፥


አብ​ር​ሃ​ምም ለቁ​ባ​ቶቹ ልጆች ሀብ​ትን ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ገና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከልጁ ከይ​ስ​ሐቅ ለይቶ ወደ ምሥ​ራቅ ሀገር ሰደ​ዳ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቅህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀኝ እጁ ይጋ​ር​ድህ።


ድዳ​ን​ንም፥ ቴማ​ን​ንም፥ ሮስ​ንም፥ ፊታ​ቸ​ውን የሚ​ከ​ተ​ቡ​ትን ሁሉ፤


የዓ​ረብ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድረ በዳ የሚ​ቀ​መጡ የድ​ብ​ልቅ ሕዝብ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም ሁሉ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios