Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ ሞሳ ባለ በጎች ነበር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ መቶ ሺህ የጠ​ጕር አውራ በጎ​ች​ንና መቶ ሺህ ጠቦ​ቶ​ችን ይገ​ብ​ር​ለት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዚህ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ ሞሳ በግ ያረባ ነበር፤ እርሱም መቶ ሺሕ ጠቦትና የመቶ ሺሕ አውራ በግ ጠጕር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የሞዓብ ንጉሥ ሜሻዕ በግ አርቢ ነበር፤ በየዓመቱም አንድ መቶ ሺህ ጠቦትና የአንድ መቶ ሺህ በጎች ጠጉር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሞአብ ንጉሥ ሜሻዕ በግ አርቢ ነበር፤ በየዓመቱም አንድ መቶ ሺህ ጠቦትና የአንድ መቶ ሺህ በጎች ጠጒር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የሞዓብም ንጉሥ ሞሳ በግ አርቢ ነበረ፤ ለእስራኤልም ንጉሥ የመቶ ሺህ ጠቦትና የመቶ ሺህ አውራ በጎች ጠጕር ይገብርለት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 3:4
11 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም በከ​ብት፥ በብ​ርና በወ​ርቅ እጅግ በለ​ጸገ።


ዳዊ​ትም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን መታ፤ በም​ድ​ርም ጥሎ በገ​መድ ሰፈ​ራ​ቸው፤ በሁ​ለ​ትም ገመድ ለሞት፥ በአ​ን​ድም ገመድ ለሕ​ይ​ወት ሰፈ​ራ​ቸው፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።


ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮች አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ጠበ​ቀው።


ሞዓ​ብ​ንም መታ፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።


በም​ድረ በዳ​ውም ግን​ቦ​ችን ሠራ፤ ብዙ ጕድ​ጓ​ድም ማሰ፤ በቆ​ላ​ውና በደ​ጋው ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​ትና፤ ደግ​ሞም እርሻ ይወ​ድድ ነበ​ርና በተ​ራ​ራ​ማ​ውና በፍ​ሬ​ያ​ማው ስፍራ አራ​ሾ​ችና የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞች ነበ​ሩት።


ከብ​ቶ​ቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመ​ሎች፥ አም​ስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አም​ስት መቶም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት፤ ሥራ​ውም በም​ድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በም​ሥ​ራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛ​ውን ለኢ​ዮብ ባረከ፤ መን​ጋ​ዎ​ቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድ​ስት ሺህም ግመ​ሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬ​ዎች፥ አንድ ሺህም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ።


እን​ዲሁ ለስ​ምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ ምኞ​ቴን ሁል​ጊዜ ትሰ​ጠኝ ዘንድ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos