እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
ኤርምያስ 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም ኢየሩሳሌምን የእግዚአብሔር ዙፋን ብለው ይጠሩአታል፤ አሕዛብም ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ወደ ኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉውን እልከኛ ልባቸውን ተከትለው አይሄዱም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን፣ ‘የእግዚአብሔር ዙፋን’ ብለው ይጠሯታል፤ መንግሥታትም ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ለማክበር በኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ የክፉ ልባቸውንም እልኸኝነት ከእንግዲህ አይከተሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን የጌታ ዙፋን ብለው ይጠሩአታል፥ በጌታ ስም አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሷ ወደ ኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉውን እልኸኛ ልባቸውን ተከትለው አይሄዱም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ዘመን ኢየሩሳሌም ራስዋ ‘የእግዚአብሔር ዙፋን’ ተብላ ትጠራለች፤ ሕዝብም ሁሉ እኔን ለማምለክ በዚያ ይሰበሰባሉ። ከዚያን በኋላ እልኸኛና የክፉ ሐሳብ ምንጭ የሆነውን ልባቸውን አይከተሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን የእግዚአብሔር ዙፋን ብለው ይጠሩአታል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርስዋ ይሰበሰባሉ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉውን እልከኛ ልባቸውን ተከትለው አይሄዱም። |
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
ከሌላም ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን ለእርሱም ባሪያዎች የሆኑትን፥ የእግዚአብሔርንም ስም የወደዱትን፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎቹ የሆኑትን፥ “ሰንበታቴን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፥ በቃል ኪዳኔም ጸንተው የሚኖሩትን ሁሉ፥
በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ። መቅሠፍትም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ኀይለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመጣል።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ ምስጋናውም ቤቱን ሞልቶት ነበር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው?
“ሥራቸውንና አሳባቸውን ዐውቄአለሁ፤ እነሆም እኔ እመጣለሁ፤ አሕዛብንና ልሳናትንም ሁሉ እሰበስባለሁ፤ እነርሱም ይመጣሉ፤ ክብሬንም ያያሉ።
የእስራኤል ልጆች ቍርባናቸውን በምስጋና ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚያመጡ፥ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፥ በፈረሶችና በሰረገሎች፥ በአልጋዎችና በበቅሎዎች፥ በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፥ ከአሕዛብ ሁሉ ወደ ተቀደሰችው ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።
እነርሱ ሁሉ ግን በክፉ ልባቸው እልከኝነት ሄዱ እንጂ አልሰሙም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ ስለዚህ ያዘዝኋቸውን እነርሱም ያላደረጉትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ አመጣሁባቸው።”
ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ ይቅር እላቸዋለሁ፥ ሁላቸውንም በርስታቸው፥ እያንዳንዳቸውንም በምድራቸው አኖራቸዋለሁ።
በበዓል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ ፈጽመው ቢማሩ፥ በዚያ ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።
ስለ ስምህ ብለህ ተመለስልን፤ የክብርህንም ዙፋን አታጥፋ፤ ከእኛ ጋርም ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ እንጂ አታፍርስ።
እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ ፍላጎት ሄዳችኋል፤ እኔንም አልሰማችሁም።
ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ።
እነርሱ ግን፥ “እንጨክናለን፤ ክዳታችንን ተከትለን እንሄዳለን፥ ሁላችንም ክፉ ልባችንን ደስ የሚያሰኛትን እናደርጋለን” አሉ።
“እኔም፦ ይሁን አልሁ፤ በወንዶች ልጆች መካከል እሾምሃለሁ፤ አሕዛብን የሚገዛ ሁሉን ቻይ የሆነ የእግዚአብሔርን ርስት የተመረጠችውን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ አባቴ ትለኛለህ፤ ከእኔም አትመለስም አልሁ ብለሃልና።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ ሀገር በከተሞችዋ፦ የጽድቅ ማደሪያ ሆይ! የቅድስና ተራራ ሆይ! እግዚአብሔር ይባርክህ የሚል ነገርን እንደ ገና ይናገራሉ።
ይህችም ከተማ እኔ የምሠራላቸውን በጎነት ሁሉ በሚሰሙ፥ እኔም ስላመጣሁላቸው በጎነትና ሰላም ሁሉ በሚፈሩና በሚደነግጡ አሕዛብ ሁሉ ፊት ለደስታ፥ ለክብርና ለገናንነት ትሆናለች።”
ሕያው እግዚአብሔርን! ብሎ በእውነትና በቅንነት፤ በጽድቅም ቢምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤ በኢየሩሳሌምም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
ነገር ግን በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ፤ ወደፊትም ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
በራሳቸውም በላይ ከአለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፤ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ።
እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ይህ ነው። ዳግመኛም የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው በአለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።
ዙሪያዋም ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማዪቱ ስም፦ ‘እግዚአብሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠራል።”
በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።
እርሱም በዘርፉ ይሁንላችሁ፤ ትመለከቱታላችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ታስባላችሁ፤ ታደርጉአቸውማላችሁ፤ እነርሱን በመከተል ያመነዘራችሁባትን የሕሊናችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ አትከተሉ።
እግዚአብሔርን ሲያውቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ አላከበሩትም፤ አላመሰገኑትምም፤ ነገር ግን ካዱት፤ በአሳባቸውም ረከሱ፤ ልቡናቸውም ባለማወቅ ጨለመ።
“ምስጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛና ለልጆቻችን ለዘለዓለም ነው።
መስፍኑ ግን ከሞተ በኋላ ዳግመኛ ተመልሰው ከአባቶቻቸው ይልቅ እጅግ ይበድሉ፤ ነበር፤ ሂደውም ሌሎች አማልክትን ተከትለው ያመልኳቸው ነበር፤ ይሰግዱላቸውም ነበር፤ ክፋታቸውንም አይተዉም ነበር፤ ከክፉ መንገዳቸውም አይመለሱም ነበር።