Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 87 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የቆሬ ልጆች የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር። ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በማ​ኸ​ላት ለመ​ዘ​መር የይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው የኤ​ማን ትም​ህ​ርት።

1 የድ​ኅ​ነቴ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በቀ​ንና በሌ​ሊት በፊ​ትህ ጮኽሁ፤

2 ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮ​ህ​ንም ወደ ልመ​ናዬ አዘ​ን​ብል፤

3 ነፍሴ መከ​ራን ጠግ​ባ​ለ​ችና፥ ሕይ​ወ​ቴም ለሞት ቀር​ባ​ለ​ችና።

4 ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ተቈ​ጠ​ርሁ፥ ረዳ​ትም እን​ደ​ሌ​ለው ሰው ሆንሁ።

5 እንደ ተገ​ደ​ሉና በመ​ቃ​ብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ደ​ማ​ታ​ስ​ባ​ቸው በሙ​ታን መካ​ከል የተ​ጣ​ልሁ ሆንሁ፤ እነ​ርሱ ከእ​ጅህ ርቀ​ዋ​ልና።

6 በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታ​ች​ኛው ጕድ​ጓድ አስ​ቀ​መ​ጡኝ።

7 በእኔ ላይ ቍጣህ ጸና፥ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ሁሉ በእኔ ላይ አመ​ጣህ።

8 የሚ​ያ​ው​ቁ​ኝን ከእኔ አራ​ቅህ፤ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ርኩስ አደ​ረ​ግ​ኸኝ፤ ያዙኝ፥ መው​ጫም የለ​ኝም።

9 ዐይ​ኖቼም በች​ግር ፈዘዙ፤ አቤቱ፥ ሁል​ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ እጆ​ቼንም ወደ አንተ ዘረ​ጋሁ።

10 በውኑ ለሙ​ታን ድን​ቅን ታደ​ር​ጋ​ለ​ህን? ወይስ ያመ​ሰ​ግ​ኑህ ዘንድ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች ያነ​ሡ​አ​ቸ​ዋ​ልን?

11 በመ​ቃ​ብ​ርስ ውስጥ ያሉት ቸር​ነ​ት​ህን፥ እው​ነ​ት​ህ​ንስ በሞት ስፍራ ይና​ገ​ራ​ሉን?

12 ተአ​ም​ራ​ትህ በጨ​ለማ ይታ​ወ​ቃ​ልን? ቅን​ነ​ት​ህስ በም​ድር ተረ​ሳን?

13 አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፤ በጥ​ዋት ጸሎቴ ወደ አንተ ትድ​ረስ።

14 አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ለምን ትጥ​ላ​ለህ? ፊት​ህ​ንስ ከእኔ ለምን ትመ​ል​ሳ​ለህ።

15 እኔ ድሃ ነኝ፥ ከሕ​ፃ​ን​ነቴ ጀምሮ ደከ​ምሁ። ከፍ ከፍ ካልሁ በኋላ ተዋ​ረ​ድሁ፥ ተና​ቅ​ሁም።

16 መቅ​ሠ​ፍት በላዬ አለፈ፥ ግር​ማ​ህም አስ​ደ​ነ​ገ​ጠኝ።

17 ሁል​ጊዜ እንደ ውኃ ከበ​ቡኝ፥ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ያዙኝ።

18 ወዳ​ጆ​ቼ​ንና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቼን ዘመ​ዶ​ቼ​ንም ከች​ግሬ የተ​ነሣ ከእኔ አራ​ቅህ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos