የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን፥ “ከእርሱ ጋር ውረድ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ” ብሎ ነገረው። ኤልያስም ተነሥቶ ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።
ኢሳይያስ 51:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ነኝ፤ የማጽናናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እንግዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የማጽናናችሁ እኔ፣ እኔው ብቻ ነኝ፤ ሟች የሆኑትን ሰዎች፣ እንደ ሣር የሚጠወልጉትን የሰው ልጆች ለምን ትፈራለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፥ እኔ ነኝ፤ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ስለምን ትፈራለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ፤ ታዲያ እንደ ሣር የሚጠወልገውንና መሞት ያለበትን ሰውን የምትፈሩት ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፥ እኔ ነኝ፥ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ትፈራ ዘንድ አንተ ማን ነህ? |
የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን፥ “ከእርሱ ጋር ውረድ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ” ብሎ ነገረው። ኤልያስም ተነሥቶ ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ደስ አሰኝሻለሁ፤ ባድማሽንም ሁሉ ደስ አሰኛለሁ፤ ምድረ በዳሽንም እንደ ዔድን፥ በረሃዎችሽንም እንደ እግዚአብሔር ገነት አደርጋለሁ። ደስታና ተድላ እምነትና የዝማሬ ድምፅ በውስጧ ይገኝባታል።
ሐሰት የተናገርሽው፥ እኔንም ያላሰብሽው፥ በልብሽም ነገሩን ያላኖርሽው ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔም ዝም አልሁሽ፤ አንቺም አልፈራሽኝም።
የተወደደችውን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠች ብዬ እጠራት ዘንድ፥ አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፥
እንዲህም አለኝ፥ “ይህ ሕዝብ፦ ከባድ ነው የሚለውን ሁሉ፦ ከባድ ነው አትበሉ፤ መፈራታቸውንም አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
ንጉሡም ሴዴቅያስ ኤርምያስን፥ “ወደ ከለዳውያን በኰበለሉ በአይሁድ እጅ አሳልፈው ይሰጡኛል፤ እነርሱም ያፌዙብኛል ብዬ እፈራለሁ” አለው።
እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በሀገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋልና።
አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥ፥ አትፍራቸው፤ ቃላቸውንም አትፍራ፤ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።
በይሁዳ፥ በሰማርያና በገሊላ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ጸንተው ኖሩ፤ ሕዝቡም በመንፈስ ቅዱስ አጽናኝነት በዙ።
ሳኦልም ሳሙኤልን፥ “ሕዝቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላቸውንም ስለ ሰማሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና የአንተን ቃል በመተላለፍ በድያለሁ።
በፊቱም መልኩን ለወጠ፤ በዚያችም ቀን አመለጠ። በከተማውም በር ከበሮ ይዞ በእጁ መታ፤ በበሩም መድረክ ላይ ተንፈራፈረ፤ ልጋጉም በጢሙ ላይ ይወርድ ነበር።