ኢሳይያስ 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ድነቴም ሆኗል።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እነሆ፥ አምላክ መድሃኒቴ ነው፥ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፥ መድኃኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜ አልፈራም ትላለህ። Ver Capítulo |